ፈረሰኞቹ የሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቁ።

በአሁኑ ሰዓት በሸራተን ሆቴል መግለጫ እየሰጡ ያሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ቀደም ሲል ጋናዊያኖቹን ተጫዋቾች አጥቂው አልፍሬድ ሜንሳህ እና ተከላካዩን ኬልቪን ኤዶን ማስፈረማቸውን የነገርኳችሁ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን አሳውቀዋል።
አይቮሪኮስታዊው አማካይ ሦስተኛው ፈራሚ ሆኗል። የ29 አመቱ ካርተር አሂሮ በአይቮሪኮስቱ አሴክ ሚሞሳ ለቡሩኪናፋሶው ራሂሞ ፣ ለኮንጎው ዲሲ ሞቴማ ፔምቤ ፣ ለኦማኖቹ ሶሀር ፣ ባህራ ክለብ ፣ አልናስር ፣ ለሊባኖሱ ሬሲንግ ቤሩት እና ሳፋ ቤሩት የተጫወተው አዲሱ የፈረንጆቹ አመት ሲገባ ክለብ አልባ የነበረው ተጫዋቹ መጃረሻው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል።
ሌላኛው ፈራሚ ኮንጓዊዊ ክሪስት ቶሉንጋ ነው።
የ20 ዓመት ዕድሜ አለው የተባለው ወጣቱ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ለሀገሩ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት በሀገሩ ለሚገኘው ዲያብሌስ ኖይሪስ እና ለአልጄሪያው ፓራዱ ክለቦች ተጫውቶ መዳረሻው ኢትዮጵያ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ