መነሻ ገጽ ዜናዎች አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕናም ወሳኝ ድል አግኝተዋል። የኢትዮጵያ ቡና እና መቻል ጨዋታ ግን 1ለ1 ተጠናቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ መቐለ 70 እንደርታ ያገናኘው ጨዋታ ፈረሰኞቹ ከሦስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሱበትን ወሳኝ ድል አሳክተዋል። ከዕረፍት በፊት ግለቱ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ በነበረው ጨዋታ 83ኛው ደቂቃ ላይ ተመስገን ተስፋዬ በሀብታሙ ጉልላት ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ በዕለቱ ዋና ዳኛ ዳንኤል ይታገሱ ለማጣት የተገደዱት መቐለዎች 89ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስተናግደዋል።

ብርሀኑ አሻሞ በረጅሙ ወደ ሳጥን ውስጥ ያሻገራትን ኳስ ብሩክ አለማየሁ በግንባር ገጭቶ ከጊት ጋር ታግሎ ቯይ ኩዌት ያመቻቸውን ኳስ ፀጋ ከድር ተፈጥሯዊ ባልሆነው የቀኝ እግሩ መሐመድ ዛጉዌ መረብ ላይ ጎል በማስቆጠር ቡድኑ መሪ ሲያደርግ ግብ አስቆጥሮ ደስታውን ለመግለፅ መለያውን በማውለቁ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ለመውጣት ቢገደድም ጨዋታው ግን በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሽንፈት ቢያስተናግድ አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን ሊያጣ ይችል የነበረው ሀድያ ሆሳዕና ወሳኝ ሦስት ነጥብን አሳክቷል። 64ኛው ደቂቃ ላይ ሔኖክ አርፊጮ ከማዕዘን ሲያሻማ ተጨራርፋ ኳስን የሀዋሳው ተከላካይ ፍቃደስላሴ ደሳለኝ በእጅ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ሔኖክ አርፊጮ ከመረብ በማሳረፍ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ነብሮቹ 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሰዋል።

አዳማ ከተማ ከአስር ጨዋታ በኋላ በጎል ተንበሽብሾ ወደ ድል ተመልሷል። 9ነኛው ደቂቃ ላይ አቤኔዘር ሲሳይ ከበሀይሉ ግርማ ታግሎ ያስጣለውን ኳስ አምበሉ ሀይደር ሸረፋ ከሳጥን ውጪ እጅግ አስገራሚ ጎልን ሪችሞንድ አይ መረብ ላይ ሲያሳርፍ 25ኛው ደቂቃ ላይ አቤኔዘር ሲሳይ በድንቅ ዕይታ ሰንጥቆ የሰጠውን ቢኒያም አይተን ሁለተኛ ጎል በማድረግ አዳማን 2ለ0 መሪ መሆን እንዲችል አስችሏል። ምድረገነት ሽረዎች ፀጋአብ ዮሐንስ 42ኛው ደቂቃ ላይ አቡበከር ሳኒ ላይ በሰራው ጥፋት በዕለቱ ዳኛ በላይ ታደሠ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኗል።

በቀይ ተጫዋች አጥተው በቁጥር እና በጎል ብልጫ የተወሰደባቸው ምድረገነት ሽረዎች ከዕረፍት መልስ 58ኛው ደቂቃ ሌላ ጎል ተቆጥሮባቸዋል። አብዱልከሪም መሐመድ ወደ ቀኝ የሰጠውን ኳስ አቡበከር ሳኒ የግብ ዘቡን ሪችሞንድ አይ ከጎል ክልሉ ለቆ መውጣትን በመመልከት እጅግ አስደናቂ ሦስተኛ ጎልን ለአዳማ ሲያስቆጥር 63ኛው ደቂቃም በሀይሉ ግርማ ሳጥን ውስጥ በአቤኔዘር ሲሳይ ላይ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠን የፍፁም ቅጣት ምት ዳዋ ሆቴሳ ማሳረጊያ በማድረግ ጨዋታው በአዳማ ከተማ 4ለ0 አሸናፊነት ተደምድሟል።

መቻል ወደ ሊጉ መሪ ይበልጥ የሚጠጋበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል። ኢትዮጵያ ቡናን ከመቻል ባገናኘው የዕለቱ የማሳረጊያ ጨዋታ 16ኛው ደቂቃ ላይ አቡበከር አዳሙ ከቀኝ ወደ ውስጥ ያሻገረውን ኳስ ቢኒያም ጌታቸው በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር አጋማሹን ከተቀላቀለ በኋላ አምስተኛ ጎሉ አድርጎ ቡናማዎቹ መሪ ቢሆኑም 21ኛው ደቂቃ ከአለምብርሀን ተነስታ ወደ ሳጥን ተሻምታ በረከት ደስታ መቶ ራምኬልን ነክታ ስትመለስ ኮሊንስ ኮፊ ወደ ጎል መቶ አቆጣጫ ልትስት የነበረች ኳስን ብሩክ ማርቆስ ተንሸራቶ ዳላንድ ኢብራሂም መረብ ላይ በማሳረፍ ጨዋታው 1ለ1 መጠናቀቅ ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...