የሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔው አሰልጣኝ ሪካርዶ ሞንሳንቶ ከጨዋታው በኋላ ምን አሉ ?
“በመጀመሪያ ለደጋፊው እና ለተጫዋቾች ያለኝን ክብር እንዲሁም የህዝቡን እንግዳ ተቀባይነት አደንቃለሁ እናም በልቤ ውስጥ ትኖራላችሁ ፤ አልረሳችሁም።

“በመቀጠል ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን አላችሁ። እኔን የገረመኝ ግን እንዲህ አይነት ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን እያላችሁ በቅድመ ማጣሪያው ላይ መገኘታችሁ ነው።
“አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ5 አመት ከሀገሩ ውጭ ተሰዶ እየተጫወተ እንደሆነ እናውቃለሁ ልክ እንደ እኛ ማለት ነው። እኛም ለ 4 አመት ያህል በሜዳችን አልተጫወትንም።
“ከዚህ በፊት ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጫውተን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ነው የተሸነፍነው ጎሏም በፔናልቲ ነው ያገቡብን። ጋና እኮ እነ ቶማስ ፓርቴ እና አንድሬ አዩ አይነት ከዋክብት የያዘች ቡድን ናት ግን በ1 ጎል ብቻ ነው ያሸነፉን። ከአልጀሪያ ጋር ተጫውተን 2 ለ 1 የተረታነው። ከእስራኤል ጋርም የወዳጅነት ተጫውተን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸነፈናል። በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ግን በጣም ጠንካራ ተፎካካሪዎች ነበርን።
“ወደ እናንተ ስመጣ ጥሩ ጥሩ ተጫዋቾች አሏችሁ በብዙዎቹ ተጫዋቾች ብቃት ተደንቂያለሁ ፣ ስማቸውን አላውቀውም ግን በተለይ 17 (ቸርነት ጉግሳ ፣ 10 ( አቤል ያለው) እና 9 ቁጥር (መስፍን ታፈሠ) በጣም ምርጥ ተጫዋቾች ናቸው። እውነት እውነት ለመናገር ፖርቹጋል ውስጥ ቢሄዱ የመጀመሪያ ሊግ ውስጥ መጫወት የሚችሉ ናቸው።” ሲሉ ተናግረዋል።
አስተያየት ይስጡ