መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ዋልያዎቹ ወደ ምድብ ማጣሪያው መግባታቸውን አረጋግጠዋል
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ ወደ ምድብ ማጣሪያው መግባታቸውን አረጋግጠዋል

አጋራ
አጋራ

ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን በአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ መርሀግብን ድሬዳዋ ላይ ያደረጉት ዋልያዎቹ 1ለ0 ሲረቱ በድምር ውጤት ደግሞ 4ለ0 አሸንፈው ወደ ምድብ ማጣሪያው አልፈዋል።

እጅግ በተጋጣሚው ሜዳ ላይ ረጅሙን ደቂቃ ያሳለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጎል ማስቆጠር የቻለው ገና 7ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። ከቀኝ መስመር አቅጣጫ መስፍን ታፈሠ ከሰራው ግሩም የእግር ስራ በኋላ ወደ ውስጥ የሰጠውን ኳስ ቸርነት ጉግሳ ወደ ጎልነት ለውጦ ዋልያውን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ሳኦቶሚዎች ኳስን ሲያገኙ ጥቂት ለማጥቃት ከሚያደርጉት ፍሬ አልባ ማጥቃት በስተቀር በኢትዮጵያ የጨዋታ ብልጫ የተወሰደባቸው ሲሆን ተጨማሪ ጎልም ለማስተናገድ ተቃርበው ነበር። በግራ የሳጥኑ ክፍል ከነዓን ማርክነህ ወደ ጎል አክርሮ መቶ ግብ ጠባቂው ፔድሮ ማቲያስ ያዳነበት እና አቤል ያለው ከማዕዘን አሻምቶ ጋቶች በግንባር ገጭቶ በተከላካዮች ርብርብ የወጣችው አጋጣሚ አስቆጪዎቹ ሙከራዎች ነበሩ።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሲመለስ ከመጀመሪያው አጋማሽ በንፅፅር ደካማ እንቅስቃሴዎች የተበራከቱበት እና ጥራት ያላቸው ጎሎችም መፈጠር ያልቻሉበት ነበር። ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ በውስን መነቃቃት በተለይ በሽግግር አጨዋወት ተሽለው የታዩ ቢመስሉም የመጨረሻው ሜዳ ላይ ግን እጅጉን ደካሞች ሆነው ቀርበዋል። በአንፃሩ መስፍን ታፈሰን ማዕከል ባደረጉ እንቅስቃሴዎች ዋልያዎቹ ለተጨማሪ ጎሎች የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም ቢችሉም ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር ይስተዋልባቸዋው በነበሩ ድካሞች ጎሎችን መቶ ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው 1ለ0 በድምሩ ደግሞ 4ለ0 በመጠናቀቁ ኢትዮጵያ ወደ ምድብ ማጣሪያው ማለፏን አረጋግጣለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...