መነሻ ገጽ አትሌቲክስ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ በወንዶች ማራቶን ያስመዘገብናቸው ውጤቶች
አትሌቲክስዜናዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ በወንዶች ማራቶን ያስመዘገብናቸው ውጤቶች

አጋራ
አጋራ

በዓለም ሻምፕዮና ኢትዮጵያ በወንዶች ማራቶንአጠቃላይ 10 ሜዳልያዎችን ስትሰበስብ ሁለቱ ብቻ የወርቅ ናቸው ።

በአለም ሻምፕዮናው መድረክ ኢትዮጵያ እና ማራቶን ትውውቃቸው እ.ኤ.አ በ1983 ሄልሲንኪ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው የአለም ሻምፕዮና ላይ የጀመረ ነበር ። በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክሎ በብቸኝነት የተወዳደረው አትሌት ከበደ ባልቻ በ2:10:27 ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ በአለም ሻምፕዮናም ሆነ በማራቶን የመጀመሪያውን ሜዳልያ ማስገኘት ችሎ ነበር ።

በመድረኩ የመጀመሪያ ወርቅ ያገኘነው ደግሞ በ8ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ነበር ። በ2001 ካናዳ ኤድመንተን ላይ በተደረገው የዓለም ሻምፕዮና አትሌት ገዛኸኝ አበራ በ2:12:42 በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችሏል ።

ከገዛኸኝ አበራ ድል በኋላ ግን ኢትዮጵያ በመድረኩ ሌላ የወርቅ ሜዳልያ ለማግኘት 18 ዓመታትን መጠበቅ የግድ ብሏት ነበር ። ከሶስት ዓመታት በፊት በኳታር ዶሀ በተደረገው 17ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ለሊሳ ዴሲሳ ሙስነት ገረመውን አስከትሎ በ2:10:40 በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል ። በዚህም ኢትዮጵያ በኦሪገኑ የአለም ሻምፕዮና ላይ አራት አትሌቶችን ለማሳተፍ ችላለች ።

ዛሬስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገብ ይሆን ?
ቀን 10:15 ሲል በሚጀምረው ውድድር አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ደረታቸውን ላይ አድርገው ከሚሮጡ አራት አትሌቶች መካከል ሶስቱ ከዚህ ቀደም በመድረኩ ለኢትዮጵያ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችለዋል።

ከዚህ ቀደም በአለም ሻምፕዮና ላይ በወንዶች ማራቶን ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ይህን ይመስላሉ ።

የወርቅ
1. አትሌት ገዛኸኝ አበራ ( 2001 )
2. አትሌት ለሊሳ ዴሲሳ ( 2019 )

የብር
1. አትሌት ከበደ ባልቻ (1983 )
2. አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ( 2013 )
3. አትሌት የማነ ፀጋዬ ( 2015 )
4. አትሌት ታምራት ቶላ ( 2017 )
5. አትሌት ሙስነት ገረመው ( 2019 )

የነሀስ
1. አትሌት ፀጋዬ አበራ ( 2009 )
2. አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ( 2013 )
3. አትሌት ታደሰ ቶላ ( 2015 )

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...