መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አጋራ
አጋራ

የውድድር አመቱን በ42 ነጥቦች 6ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ቡናማዎቹ በዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ቀን ሁለት ተጫዋቾችን ከሰበታ ከተማ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

ሁለቱ ተጫዋቾች በሰበታ ከተማ መልካም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት የግራ መስመር ተከላካዩ ኃይለሚካኤል አደፍርስ እና አማካኙ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ሲሆኑ በቡናማዎቹ ቤት ለሶስት አመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ፈርመዋል ።

ኃይለሚካኤል አደፍርስ ከ2011 ጀምሮ እከተጠናቀቀው የውድድር አመት መጨረሻ ድረስ በሰበታ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች እና በዋናው ብሄራዊ ቡድንም መመረጥ ችሎ ነበር ። ተጫዋቹ በውድድር አመቱ 25 ጨዋታዎችን አድርጎ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ በደደቢት የታዳጊ ቡድኖች እና ዋናው ቡድን ተጫውቶ በ2013 ዓ.ም ሰበታ ከተማን መቀላቀል ችሏል ። በክለቡም ጥሩ ሁለት አመታትን ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በ2013 ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ውድድር ላይ የብሔራዊ ቡድኑ አባል ነበር ። ተጫዋቹ በውድድር አመቱ በሰበታ ከተማ 26 ጨዋታዎችን በማድረግ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...