መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 30ኛ ሳምንት መጠናቅ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 30ኛ ሳምንት መጠናቅ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል

አጋራ
አጋራ

በሳምንቱ የተመሳሳይ ሰዓት ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎም ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች ጥሪ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ እሁድ ሰኔ 26 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋቾች ዳንኤል ተሾመ(አዲስ አበባ ከተማ)፣ አብዱልባሲጥ ከማል(ሃዋሳ ከተማ) እና ጀማል ጣሰው(አዳማ ከተማ) በ5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

በ30ኛ ሳምንት አርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር ጥሪ አደርጓል።

በዚህም ለሶስት የጨዋታ ታዛቢዎች ሻለቃ በልሁ ሀይለማሪያም፣ ሰላሙ በቀለ እና አበጋዝ ነብየልዑል ሲሆን ከዳኞች ለኢንተርናሽናል ዳኛ ዶ/ር ኃይለየሱስ ባዘዘው፣ ለኢንተርናሽናል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ፣ ለፌዴራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ፣ ለፌዴራል ዳኛ ባህሩ ተካ ለፌዴራል ዳኛዮናስ ካሳሁን እና ለፌዴራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ እንዲሁም ከቡድን አባላት ለፋሲል ከነማ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ እና ለቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ ፥ ለሃዋሳ ከተማ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እና የቡድን መሪው ብርሃኑ ጤዳሞ ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እና የቡድን መሪው መሰረት ወ/ማርያም ረቡዕ ሰኔ 29 2014 ዓ.ም በተለያየ ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ጽ/ቤት እንዲገኙ ጥሪውን አስተላልፏል።

©epl

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...