“ደጋግሜ ስልክ ስደውልለት አለማንሳቱ የዲሲፕሊን ችግር በመሆኑ ከቡድኑ ውጪ አድርጌዋለሁ”
የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ” የዲሲፕሊን ችግር የለብኝም ስልኩን ለምን እንዳላነሳሁ ግን አሰልጣኝ ውበቱ በደንብ ያውቃል”
የዋሊያዎቹ አምበል ጌታነህ ከበደ
የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ የቡድኑን አምበልና የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን እየመራ ያለውን ጌታነህ ከበደን አለመምረጣቸው አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።
አሰልጣኙ እንደተናገሩት “የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋችና አምበል ቢሆንም በተደጋጋሚ ጊዜ ደውዬለት ስልኩን አንስቶ ሊያናግረኝ እንደ አምበልነቱ ልንነጋገር አልቻልንም ይሄ ደግሞ የዲሲፕሊን ችግር በመሆኑ ከቡድኑ ውጪ አድርጌዋለሁ ደጋግሜ ደውዬ አለማንሳቱ ደግሞ የዲሲፕሊን ችግር በመሆኑ ከቡድኑ ውጪ አደሰርጌዋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
ጌታነህ ከበደ ግን የአሰልጣኙን ሀሳብ እንደማይቀበለው ተናግሯል። አምበሉ እንደሚለው” ምንም አይነት የዲሲፕሊን ችግር የለብኝም በብቃቴ ካመነ እንደማንኛውም ተጨዋች ቡድኑ ውስጥ አካቶ ከጠራኝ በኋላ ወደ ሆቴል ስገባ ማናገር ይችል ነበር ይህን አላደረገም በዋናነት ግን ስልኩን ለምን እንዳላነሳው በደንብ ያውቃል። ስልክ አለማንሳቴን ከዲሲፕሊን ችግር አንጻር ከማየቱ በፊት ምክንያቱን በደንብ ያውቀዋል” ሲል ችግር እንዳለ ችግሩን ግን መግለጽ እንደማይፈልግ አስረድቷል።
ጌታነህ ከዋሊያዎቹ ለጊዜው ቢለይም ከማላዊና ከግብጽ ጋር ጨዋታ ያለባቸው ዋሊያዎቹ መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው ተመኝቶ ለአሰልጣኝ ውበቱ አሁንም ቢሆን ክብር እንዳለውና ብሄራዊ ቡድኑ የተሻለ ደረጃ እንደሚያደርሱት እምነቱ መሆኑን ገልጿል።
አስተያየት ይስጡ