መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንትን መጠናቀቅን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንትን መጠናቀቅን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል

አጋራ
አጋራ

ዳዋ ሆጤሳ እና ጌታነህ ከበደ እያንዳንዳቸው የሶስት ጨዋታዎች ቅጣት ተላልፎባቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 16 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች ወንድማገኝ ማርቆስ(ጅማ አባ ጅፋር)፣ አንተነህ ጉግሳ(ወላይታ ድቻ)፣ በኃይሉ ግርማ(ሰበታ ከተማ) እና አዲስዓለም ተስፋዬ(ሃዋሳ ከተማ) በተለያዩ የክለባቸው ጨዋታዎች አምስተኛ ቢጫ ካርድ በማየታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1,500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ እንዲሁም ፍሬዘር ካሳ(ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ጊት ጋትኩት(ሲዳማ ቡና)፣ በረከት ሳሙኤል (ሰበታ ከተማ) እና ሚሊዮን ሰለሞን(አዳማ ከተማ) አስረኛ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ሁለት ጨዋታ እንዲታገዱና የገንዘብ ቅጣት ብር 2,000 /ሁለት ሺህ/ እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፏል። በተጨማሪም ዳዋ ሆጤሳ (አዳማ ከተማ) የተጋጣሚን ቡድን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት 3 ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 3,000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ፥ ጌታነህ ከበደ(ወልቂጤ ከተማ) የዕለቱ ጨዋታ ካለቀ በኋላ የውድድር አመራሮችን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡና ስለመዝለፉ ሪፖርት የቀረበበት በፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እና ብር የ3,000 /ሶስት ሺህ/ እንዲቀጡ ተወስኗል።

በክለቦች ደረጃ የአዳማ ከተማ ክለብ 7 ተጫዋቾች እንዲሁም የሲዳማ ቡና ክለብ 6 ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ የገንዘብ ቅጣት ብር 5,000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ፥ ባህር ዳር ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች ጨዋታው ካለቀ በኋላ የክለቡን አመራሮችና ተጫዋቾች በተደጋጋሚ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበትና እንዲሁም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት አጥፍተው የተቀጡና በዚህም ደጋፊዎቹ ከድርጊታቸው አለመማራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ብር የ75,000 /ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲቀጣ ፥ ፋሲል ከነማም የክለቡ ደጋፊዎች በሳምንቱ ጨዋታቸው የዕረፍት ሰዓት ወቅት ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መልዕክት ስለማስተላለፋቸው እንዲሁም የዕለቱ ጨዋታ ካለቀ በኋላ ወደሜዳ ዘለው ስለመግባታቸው ሪፖርት የቀረበበት የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ በፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50,000 /አምሳ ሺህ/ እንዲቀጣ ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...