መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል

አጋራ
አጋራ

በ23ኛው ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ በቀዳሚነት የተደረገው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የወላይታ ድቻ ጨዋታ ግብ ሳይተስናገድበት ተጠናቋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ22ኛው ሳምንት ሀዋሳ ከተማን በረቱበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 ሁለት ለውጦችን በማድረግ ጋቶች ፓኖምን እና ቡልቻ ሹራን በናትናኤል ዘለቀ እና ሀይደር ሸረፋ ምትክ ሲያሰልፉ በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከባህርዳር ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድን በሌላኛው ግብ ጠባቂ በረከት ገነቱ ተክተው ጨዋታውን ጀምረዋል ።


በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የወላይታ ድቻን የኋላ መስመር ለማስከፈት ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በአንፃሩ ወላይታ ድቻዎች የተጋጣሚ ተጫዋቾች ክፍተቶችን አግኝተው የግብ ሙከራዎትን እንዳያደርጉባቸው በማድረግ በመከላከሉ ውጤታማ ጊዜን ሲያሳልፉ ረጃጅም ኳሶችን ፊት መስመር ላሉ ተጫዋቾች በመጣል ደግሞ የግብ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ሲታትሩ ቆይተዋል ።

የጦና ንቦቹ ንቦቹ በ7ኛው ደቂቃ ላይ በቃልኪዳን ዘላለም እና በ10ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ በምንይሉ ወንድሙ አማካኝነት ያደረጓቸው የግብ ሙከራዎች ከግቡ አናት በላይ ወጥተዋል ።

በጨዋታው የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በ13ኛው ደቂቃ ላይ የተደረገ ሲሆን ፍሪምፖንግ ሜንሱ በአማኑኤል ገብረሚካኤል ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂው ቢንያም ገነቱ መልሶበታል ።

በ17ኛው ደቂቃ ምንይሉ ወንድሙ ከርቀት ወደ ግብ የመታው ኳስ ቻርለስ ሉክዋጎ በቀ ይዞታል ።

ጨዋታው ከውሀ እረፍት መልስ ሲመለስ የፈረሰኞቹ የኳስ ቁጥጥር ከነበረው የቀጠለ ሲሆን የመሀል ተከላካዮቻቸው ሳይቀር በወላይታ ድቻ የሜዳ ክፍል ውሰጥ ተገኝተው የኳስ ቅብብሎችን በተደጋጋሚ ሲያደርጉ ነበር ። ነገር ግን የጦና ንቦቹ ጠንካራ የመከላከል ቅርፅ በየትኛውም አጋጣሚ ፈረሰኞቹ የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ እንዳይቸሉ አድርጓቸዋል ።

ሌላው በአጋማሹ የታየው በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦች መነሻ የሆነው የሄኖክ አዱኛ የቆሙ ኳሶች ውጤታማ አለመሆን ነው ። ሄኖክ በአጋማሹ ጥቂት የማይባሉ የቆሙ ኳሶችን ከማዕዘን ምትም ሆነ ከርቀት የቅጣት ምቶች ማግኘት ቢችልም ከተጫዋቹ የሚነሱ ኳሶች የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ሲሳይ ይሆኑ ነበር ።

በ39ኛው ደቂቃ ላይ ከነአን ማርክነህ ከሀብታሙ ንጉሴ ጋስ ኳስ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ወድቆ በግራ ትከሻው ላይ ባጋጠመው ጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ሌላኛው የአማካይ ክፍል ተጫዋች ሀይደር ሸረፋ ተክቶት ወደ ሜዳ ገብቷል ።
የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ግብ ተጠናቋል ።

ሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ ለቀቅ ያለ እና የግብ ሙከራዎችንም ከቀዳሚው አጋማሽ በተሻለ ያስመለከተን ነበር ። በተሻለ መነቃቃት ወደ ሜዳ የገቡት የሚመስሉት ሁለቱም ክለቦች ኳሶችን በየራሳቸው መንገድ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ቶሎ ቶሎ ሲያደርሱም ነበር ። ፈረሰኞቹ በተለይም በቀኝ መስመር በኩል ሱሌማይ ሀሚድን በደስታ ደሙ ቀይረው ከገቡ በኋላ ሳጥን ውሰጥ በመግባት የግብ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር የጣሩ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል በመልሶ ማጥቃት ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ለመድረስ ጥረቶችን ማድረግ ችለዋል ።

በአጋማሹ ቀዳሚ ሙከራ 53ኛው ደቂቃ ላይ ሱሌማን ሀሚድ በሳጥኑ የቀኝ አቅጣጫ ከሀይደር ሸረፋ የደረሰውን ኳስ ወደ ግብ መሞከር ቢችልም ያን ያህል ጠንካራ ያልነበረውን ምት በረከት መልሶታል ።

ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ ሄኖክ አዱኛ በጨዋታ እንቅስቃሴ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አማኑኤል ገብረሚካኤል በግንባር ገጭቶ በረከት መልሶት የማዕዘን ምት ሆኗል ። ከማዕዘን ምቱ የተሻገረውን ኳስ ፍሪምፖንግ በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ኳሱ ኢላማውን ባለመጠበቁ ሳይሳካ ቀርቷል ።

በ65ኛው ደቂቃ ላይ የጦና ንቦቹ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ይዘው የሄዱትን ኳስ ቃልኪዳን ዘላለም ተቀይሮ ለገባው ቢንያም ፍቅሬ አቀብሎ ቢንያም ወደ ግብ የላከው ኳስ በግብ ጠባቂው ተይዟል ።

72ኛው ደቂቃ ላይ ቃልኪዳን ዘላለም ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ ቢንያም ፍቅሬ በግንባር ገጭቶ ለምንይሉ ያደረሰውን ኳስ ምንይሉ ወደ ግብ ሞክሮ ቻርለሰ ሉክዋጎ አድኖበታል ።

ቀጣዮቹ ደቂቃዎች ፈረሰኞቹ የጦና ንቦቹን የኋላ ክፍል ለማስከፍት ስኬታማ ያልሆኑ ሙከራዎችን ያደረጉባቸው እና ተጋጣሚያቸው ደግሞ በፈጣን መልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴዎች አደገኛ አጋጣሚዎችን መፍጠር የቻሉበት ሆኖ በመጨረሻ ውሳኔዎች ክፍትተ ውጤታማ ለመሆን ያልቻሉበት ነበር ።

84ኛው ደቂቃ ላይ ናትናኤል ዘለቀ ያሻገረውን ኳስ በቸርነት ጉግሳ ግንባር ተገጭቶ የደረሰው ዳግም አርአያ ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ዘቡ ተመልሷል ።

በመጨረሻም ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት 0 – 0 በሆነ ውጤት ፍፃሜውን አግኝቷል ።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 51 በማድረስ በመሪነቱ ሲያስቀጥል ወላይታ ድቻ በበኩሉ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃውን አስጠብቆ ቀጥሏል ።

በ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ግንቦት 8 ( ሰኞ ) 10:00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን ሲገጥም ከሁለት ቀናት በኋላ ግንቦት 10 ( ረቡዕ ) በተመሳሳይ 10:00 ላይ ወላይታ ድቻ ሲዳማ ቡናን የሚገጥም ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...