መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | የፋሲል ከነማ እና የአዲስ አበባ ከነማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዲስአበባ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | የፋሲል ከነማ እና የአዲስ አበባ ከነማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከአዲስ አበባ ከነማ አገናኝቶ 2 – 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።

ፋሲል ከነማዎች በ18ኛው ሳምንት ጅማ አባጅፋርን ሲረቱ በጨዋታው ላይ ከተጠቀሙት ምርጥ 11 አንድ ለውጥ በማድረግ በናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ምትክ ሱራፌል ዳኛቸውን ሲያሰልፉ አዲስ አበባ ከነማም በሳምንቱ መከላከያን ሲረቱ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድ ቅያሪ ብቻ በማድረግ በመሀመድ አበራ ምትክ እንዳለ ከበደን አሰልፈዋል ።ፈጣን እና መልካም ሊባል በሚችል እንቅስቃሴ የተጀመረው የፋሲል ከነማ እና የአዲስ አበባ ከነማ ጨዋታ ክፍት የነበረ እና ጥሩ የኳስ ፍሰት የታየበት ነበር ።

በጨዋታው 6ኛ ደቂቃ ላይ አዲስ አበባ ከነማዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል ። አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ ጀርባውን ለግብ ሰጥቶ የነበረው ሪችሞንድ አዶንጎ በግሩም ሁኔታ ኳሱን ይዞ በመዞር በሳማኪ መረብ ላይ አሳርፎታል ።ከግቡ በኋላ አፄዎቹ በተለይም በሁለቱ መስመር ባሉ ተጫዋቾቻቸው አማካኝነት የግብ ዕድል ለመፍጠር ቢጥሩም አዲስ አበባ ከነማዎች በመከላከሉ ጥሩ መሆናቸው በቀላሉ ዳንኤል ተሾመን መፈተን እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ።

በ19ኛው ደቂቃ ላይም ናይጄሪያዊው አጥቂ ፋሲል ከነማን አቻ አደረገ ። በረከት ደስታን በራሳቸውን ሳጥን ውስጥ የነጠቀው አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ለሰከንዶች መረጋጋት ባለመቻሉ ኦኪኪ በፍጥነት ገብቶ የጨዋታውን ውጤት ወደ 1 – 1 የቀየረ ግብ አስቆጥሯል ።የሚገኙ ኳሶችን በፍጥነት በመስመር በኩል በማውጣት የግብ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ይደረጉ የነበሩ ጥረቶች በርካታ ቢሆኑም ግብ ጠባቂዎቹን የፈተነ ተመልካችን ከመቀመጫው ቁጭ ብድግ የሚያደርግ ሙከራ ለመመልከት ደቂቃዎችን መጠበቅ የግድ ብሎ ነበር ።

34ኛው ደቂቃ ላይ በሚያሻግራቸው እና በጠንካራ ኳሶቹ የሚታወቀው ሱራፌል ዳኛቸው ከርቀት ወደ ግብ የመታው እና በዳንኤል ተሾመ የተመለሰው ኳስ አስደናቂ ነበር ። የመጀመሪያው አጋማሽም ያለግብ በ1 – 1 ውጤት ተጠናቀቀ ።በሁለተኛው አጋማሽ ተመሳሳይ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር ። በፋሲል ከነማም ሆነ በአዲስ አበባ ከነማ በኩል የነበረው በቶሎ ወደ ግብ የመድረስ ፍላጎት ጨዋታውን ሳቢ ያደረገው ነበር ።

በአፄዎቹ በኩል በኦኪኪ አማካኝነት ከሳጥን ውጪ በተደረገ ሙከራ የአዲስ አበባ ከነማን የኋላ ክፍል መፈተን ሲጀምሩ በ57ኛው ደቂቃ ላይ በራሱ በኦኪኪ ሁለተኛ ግብ አስቆጥረዋል ።አዲስ አበባ ከነማዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት ወደ መልሶ ማጥቃት በመቀየር በሱራፌል ዳኛቸው አቀባይነት እና በኦኪኪ አፎላቢ ጨራሽነት ፋሲል ከነማ ከመመራት ወደ መሪነት እንዲመለስ አደረገው ። ፈጣን የኳስ ምልልሶች ሲያሳየን በቆየው ጨዋታ ከሙከራ ርቆ ቢቆይም በ70ኛው ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ ከነማ በኩል በረጀም ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል የደረሰውን ኳስ ፍፁም አለሙ ለእንዳለ ከበደ አድርሶት የነበረ ቢሆንም ለግቡ ቅርብ ሆኖ እንዳለ በግንባር የገጨው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል ።ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ እንዳለ ከበደ በቀኝ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ለቡድን አጋሩ ለመቀነስ ሲሞክር ከድር ኩሊባሊ እጁን ወደ ኳስ ሰንዝሮ የነበረ ሲሆን ኳሱን ግን በእጁ ሳይነካው ቢቀርም የዕለቱ የመሀል ዳኛ አለምአቀፍ ዳኝ ባምላክ ተሰማ የፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተዋል ። የፍፁም ቅጣት ምቱንም ፍፁም ጥላሁን ወደ ግብነት ቀይሮታል ።በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተለይም በተጨማሪው የባከነ 7 ደቂቃዎች ላይ ጥሩ ጥሩ የግብ ዕድሎች ቢፈጠሩም ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው 2 – 2 በሆነ ውጤት ፍፃሜውኖ አግኝቷል ።

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን 31 በማድረስ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ሲል አዲስ አበባ ከነማ በ19 ነጥብ በነበረበት 14ኛ ደረጃ ላይ የሚቆይ ይሆናል ።

በ20ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ በመጪው ማክሰኞ ቀን 9 ሰዓት ላይ ከአርባምንጭ ከነማ ሲጫወት አንድ ቀን ቀደም ብሎ በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ አዲስ አበባ ከነማ አዳማ ከነማን ይገጥማል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...