የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ መከላከያን ከሰበታ ከተማ አገናኝቶ ለስምንት ተከታታይ ጨዋታዎች ከድል ጋር ተጣልቶ የነበረውን ሰበታ ከተማን ወደ አሸናፊነት መልሷል ።
ሰበታ ከተማዎች በ16ኛው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ በሰለሞን ደምሴ ምትክ ምንተስኖት አሎን ሲያሰልፉ በመከላከያ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከአርባ ምንጭ ከተማ አቻ ሲለያዩ የነበረው ምርጥ 11 ላይ ምኑ ለውግ ሳያደርጉ ጨዋታውን ጀምረዋል ።
በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ ሊባል የሚችል የሜዴ ላይ እንቅስቃሴ የታየ ሲሆን ሰበታ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥር አንፃራዊ የበላይነተ ነበራቸው ።
በተለይም የመስመር ማጥቃቶች በዛ ብለው በታዩበች የመጀመሪያው አጋማሽ በመከላከያምጨሆነ በሰበታ በኩል የተጋጣሚን መረብ ለመድፈር ተደጋጋሚ ጥረቶቾ ቢስተዋሉም ወደ ግጓግ ቀረብ ብሎ ጠንካራ የግብ ሙከራ በማድረጉ ረገድ ደከም ብለው ታይተዋል ።
በ18ኛው ደቂቃ ላይ ቢንያም በላይ በግራ መስመር በኩል ወደ ሳጥን ይዞ የገባውን ኳስ ለተሾመ በላቸው አቀብሎት የነበረ ቢሆንም ተሾመ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል ።
በሰበታ ከተማ በኩል ደግሞ በአጋማሹ ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር የቻሉት በ23ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ። ጌቱ ሀይለማርያም ከቀኝ መስመር ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ዱሬሳ ሹቢሳ በግንባር በመግጨት ወደ ግብነት ለመቀየር ያደረገወሸ ጥረት ኳሱ ለጥቂት ከግቡ አናት በላይ በመውጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል ።
በ29ኛው ደቂቃ ላይ መከላከያዎች ሌላ ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር ችለው የነበረ ሲሆን ከቢንያም በላይ በግራ አቅጣጫ የተገኘ የቅጣት ምት ወደ ግብ ተሻግሮ ተሾመ በላቸው በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት በምንተስኖት አሎ ለጥቂት ግብ ከመሆን ድኗል ። የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ግብ ተጠናቀቀ ።
በሁለተኛው አጋማሽ ሰበታ ከተማዎች በተሻለ የኳሽ ቁጥጥር እና የማጥቃት እንቅስቃሴ የቀረቡበት ነበር ። በዚህም በተለያዩ አጋጣሚዎች የመከላከያ የተከላካይ ክፍል ለመፈተን ችለዋል ። በአንፃሩ በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚመሩት መከላከያዎች አብዛኛውን የአጋማሹን ክፍለ ጊዜ በራሳቸው ሜዳ ላይ አፈግፍገው ለመጫወት ተገደው ነበር ።
ሰበታ ከተማዎች በ63ኛው ደቂቃ ላይ በሳሙኤል ሳሊሶ አማካኝነት ከቅጣቶ በቀጥታ ወደ ግብ የሞከሩት ኳስ በመከላከያው ግብ ጠባቂ ክሌመንት ቦዬ የተመለሰ ሲሆን በ73ኛው ደቂቃ ላይም በዘካርያስ ፍቅሬ ከሳጣን ውጪ ያደረጉት የግብ ሙከራ በድጋሚ በግብ ጠባቂው ግብ ከመሆን ድኗል ።
በ83ኛው ደቂቃ ላይ ከርቀት በቅጣት ሜት ወደ ግብ የተሻገረውን ኳስ ንሲምባባ በግሩም ሁኔታ በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገውን ሙከሬ ክሌመንት ቦዬ በድንቅ ብቃት አድኖታል ። መደበኛው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ያህል ደቂቃዎች ብቻ በቀሩት ሰዓት ግን ሰበታ ከተማዎች የጨዋታውን ውጤቶ የቀየረች ግብ አስቆጥረል ። ኃይለሚካኤል አደፍርስ በሳጥኑ የግራ መስመር ወደ ግቡ ትይየሐ ለነበረው ንስባምቢ የላከው ኳስ በአጥቂው አማካኝነት በመከላከያ መረብ ላይ አርፏል ።
ጨዋታውም በዚህች ብቸኛ ግብ ተጠናቀቀ ።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም ሰበታ ነጥቡን 12 በማድረስ በጊዜያዊነት ወደ 15ኛ ደረጃ ከፍ ሲል መከላከያ በበኩሉ በነበረበት 19 ነጥብ እና 11ኛ ደረጃ የሚቆይ ይሆናል ።
በ18ኛው ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ማክሰኞ ቀን 9 ሰዓት ላይ መከላከያ አዲስ አበባን ሲገጥም ሰበታ ከተማ በበኩሉ በዕለቱ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ይገጥማል ።
አስተያየት ይስጡ