ሁለት አመታትን ያህል በብርቱካናማዎቹ ቤት መጫወት የቻለዉ ሄኖክ ኢሳያስ በዛሬው ዕለት ለጣና ሞገዶቹ ለመጫወት ፊርማዉን አኑሯል።
ከዚህ ቀደም ለጅማ አባጅፋር ፣ ወላይታ ድቻ ፣ መቀለ 70 እንደርታ እና ድሬዳዋ ከተማ መጫወት የቻለዉ ሄኖክ በዛሬው ዕለት ደግሞ በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለሚመራዉ ባህርዳር ከተማ ቀጣዩቹን አመታት ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም በ15 ጨዋታዎች 20 ነጥብ በመሰብሰብ 7 ደረጃ ላይ በመቀመጥ የመጀመሪያዉን ዙር ያጠናቀቁት ባህርዳር ከተማዎች በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ