መነሻ ገጽ አፍሪካ “አቡበከር ናስር በቅርቡ ከሀገር ወጥቶ እንደሚጫወት እርግጠኞች ነን” ዘአናሊስት
አፍሪካአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

“አቡበከር ናስር በቅርቡ ከሀገር ወጥቶ እንደሚጫወት እርግጠኞች ነን” ዘአናሊስት

አጋራ
አጋራ

በጉጉት የሚጠበቀዉ 33ኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀምር የአንድ ቀን እድሜ ብቻ የቀረዉ ሲሆን በዚህም በአዘጋጇ ሀገር ካሜሩን ምድብ የሚገኙት ዋልያዎቹ ልምምዳቸዉን አጠናክረው ቀጥለዉ ለነገዉ ጨዋታ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

ከአፍሪካ ዋንጫው መጀመር አስቀድሞ የተለያዩ የሚዲያ አካላት በአፍሪካ ዋንጫዉ ላይ ተሳታፊ ስስሆኑት ሀገራት እንዲሁም ዉድድሩ ላይ ይደምቃሉ ተብለዉ የሚጠበቁትን ተጫዋቾች በመጠቆም ላይ የሚገኙ ሲሆን ፤ በዚህም ዘ አናሊስት የተባለው ድህረገጽ ስለ ዋልያዎቹ የቡድንን ስብስብ ፣ ስለ አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ፣ ስለ አጥቂዎቹ አቡበከር ናስር እና ጌታነህ ከበደ ተከታዩን ሀሳብ አስነብቧል።

ዘገባው ካነሳቸዉ በርካታ ጉዳዮች መካከልም:-

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ በአብዛሀኛዉ ተጫዋቾቹን የመረጠው ከሀገር ዉስጥ ሊግ እንደሆነ እንዲሁም በማጣሪያው ዉድድር ላይ ጥሩ ተፎካካሪ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ቡድኑ ከሀገር ወጥቶ ሲጫዎት ደካማ መሆኑን ጠቁሟል። ለዚህም አብዛኞቹ ብሔራዊ ቡድኖች ከሀገራቸው ወጥተዉ ሲጫወቱ ይበልጥ መከላከል ላይ ሲያተኩሩ በአንፃሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በድፍረት ኳስን በመቆጣጠር አጥቅቶ ለመጫዎት እንደሚሞክር እና ይሄም ተወዳጅ እንደሆነ አስነብቧል።

በዘገባውም ኬፕ ቨርዲን አሸንፎ ከካሜሩን እና ቡርኪናፋሶ ጋር ነጥብ መጋራት የአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ዋነኛ ዕቅድ ሊሆን እንደሚችል የጠቆመ ሲሆን በተጫዋቾች በኩል ደግሞ ወጣቱ አጥቂ አቡበከር ናስር እጅግ ፈጣን እና ጥሩ የቴክኒክ ችሎታ ያለዉ እንደሆነ እና ከፊት መስመር አጥቂዉ ጌታነህ ከበደ ጋር ጥሩ ጥምረት እንደሚኖራቸዉ እንደሚጠበቅ ገልጿል። ከዘህ ጋር ተያይዞም ወጣቱ አጥቂ አቡበከር ናስር በቅርቡ ከሀገር ወጥቶ እንደሚጫት እንዲሁም ለዚህ አቅሙ እንዳለዉ አስነብቧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...