አጠቃላይ ስለጨዋታው….
“ደቡብ አፍሪካ ትልቅ ቡድን ነዉ ይሄ የታወቀ ነዉ። ለዛም ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ተጭነዉን ለመጫወት ሞክረዋል ሀይልን ቀላቅለዉ በመጫወት የኛን የጨዋታ መንገድ ሲያበላሹም ነበር።”
“ከእረፍት በፊት የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችለን ነበር ነገር ግን ማስቆጠር አልቻልንም ይሄ ደግሞ አንዱ ክፍተታችን ነበር። ግብ ከተቆጠረብን በኋላም በተቻለ መጠን አቻ ለመሆን ጥረት አድርገን ተሳክቶልን ነበር ፤ ቢሆንም ግን በተደጋጋሚ በሰራናቸዉ ቀላል ስህተቶች ሶስት ጎል ልናስተናግድ ችለናል። ዛሬ ለኛ በጣም ከባድ ቀን እንደነበር ነዉ የሚሰማኝ እሰከዛሬ በነበርን ጨዋታ ሶስት ጎል አልተቆጠረብንም።”
“ከወትሮዉ የተለየ ጨዋታ ነበር ማለት ባይቻልም በተወሰኑ ጥቃቅን ስህተቶች ዉጤቱ ከእጃችን ወጥቷል። በአጠቃላይ የነበሩብንን ክፎተቶች ለመመልከት ሞክረን ለማክሰኞዉ ጨዋታ የምንዘጋጅ ይሆናል።”
“ጎል ማስቆጠር ካልቻልን እና በቀላሉ ግብ የሚቆጠርብን ከሆነ ያዉ መሸነፋ ተገቢ ነዉ ብየ ነዉ የማስበዉ። በቀላል ስህተቶች ዋጋ ከፍለናል ጎሎች የሚቆጠሩብን በቀላል ስህተቶች ነበር እነሱን ማረም ከቻልን ዉጤት እናመጣለን ብየ አስባለሁ።”
ስለቀጣዩ ጨዋታ….
“ቀጣዩን ጨዋታ ከሜዳችን ዉጭ አሸንፈን ዉጤት ለማምጣት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ከዛ ባለፈ ግን በዚህ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዉድድር የገጠምናቸዉ ጋና ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ከኛ በደረጃ የተሻሉ ናቸዉ። ከእነረሱ የምናገኘዉ ለምድ በዉድድሩለማለፍ ከምናደርገው ጥረት ባለፈ ለኛ በጣም ጠቀሜታ አለዉ።”
የነጥብ ልዩነቱ ስለመስፋቱ…
“ከመሪዎቹ ጋር የአራት ነጥብ ልዩነት አለን በጥብ ደረጃ ካሰብን በአሁኑ ሰዓት ላይ ስለማለፍ ለማናገር ትንሽ ከባድ ይመስለኛል ያም ሆኖ ግን ዉድድር ዉስጥ እሰካለን ድረስ እሰከመጨረሻዉ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን።”
አስተያየት ይስጡ