መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ዋልያዎቹ በዛሬዉ ጨዋታ ከስምንት አመታት በፊት የሰሩትን ገድል ይደግሙት ይሆን !!
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በዛሬዉ ጨዋታ ከስምንት አመታት በፊት የሰሩትን ገድል ይደግሙት ይሆን !!

አጋራ
አጋራ

ለኳታሩ የ2022 የአለም ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሰባት ከጋና ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዙምባቡዌ ጋር ተደልድለዉ የሚገኙት ዋልያዎቹ በዛሬዉ ዕለት ከቀኑ በ10:00 ሰዓት እንዲሁም በመጪው ማክሰኞ ከሜዳቸው ዉጭ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ከዛሬዉ ጨዋታ አስቀድሞ ትላንት ረፋድ ላይ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ጨዋታዉ በሚደረግበት የባህርዳር ስታዲየም የሰሩት ዋልያዎቹ ለዛሬዉ ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ስለመሆናቸው እና ሁሉም ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ትላንት አመሻሽ በኩሪፍቱ ሪዞርት በነበረዉ ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸዉን መዘገባችንም ይታወሳል።

በዛሬዉ ወሳኝ ጨዋታም ከስምንት አመታት በፊት በተመሳሳይ በአለም ዋንጫ የማጣሪያ በአንድ ምድብ ተደልድለዉ የነበሩት ሁለቱ ሀገራት ዳግም የሚገናኙ ሲሆን ያኔ የመጀመሪያውን ጨዋታ ዋልያዎቹ ከሜዳቸዉ ዉጭ ተጫዉተዉ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ሲያጠናቅቁ የመልሱን ጨዋታ በአዲስአበባ ስታዲየም በጌታነህ ከበደ እና ፖርከር በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠሯቸዉ ጎሎች ታግዘዉ 2ለ1 ማሸነፋቸዉ ይታወሳል። ያኔ ከነበረው የዋልያዎቹ ስብስብም በአሁኑ ሰዓት ጌታነህ ከበደ ፣ ጀማል ጣሰዉ እና ሽመልስ በቀለ የሚገኙ ሲሆን ፤ ከምድቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አስራ ስድስት ተጥቦችን በመሰብሰብ የአንደኝነት ደረጃን በመያዝ የአፍሪካ ምርጥ አስር ብሔራዊ ቡድኖች ተርታ መሰለፍ ችለዉ ነበር ፤ ዛሬስ ያንን ታሪክ የሚደግሙት ይሆን…..?

በተያያዘም በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኙት ጋና እና ዚምባቡዌ ምሽት 1:00 ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ፤ ምድቡን ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ ስትመራ ጋና እና ኢትዮጵያ በእኩል ሶስት ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ፤ ዚምባቡዌ ደግሞ በአንድ ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...