በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዉ በአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ጥሩ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ጅማዎች ተጨማሪ የመስመር ተጫዋች ወደ ስብሰባቸው መቀላቀላቸው ታዉቋል።
ከቀድሞ ክለቡ ባህርዳር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየዉ መስመር ተከላካዩ ሚኪያስ ግርማ በመጨረሻም ማረፊያዉ ጅማ አባጅፋር መሆኑ ታዉቋል።
ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ አራዳ ክ/ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ መጫወት የቻለዉ ሚኪያስ ግርማ ከዘንድሮው የዉድድር አመት አንስቶ በጅማ መለያ የምንመለከተው ሌላኛዉ ተጫዋች ሆኖአል ።
አስተያየት ይስጡ