በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በወርሀ መጋቢት ከክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዲሲፕሊን ግድፈት ፈፃሟል በሚል ታግዶ የቆየዉ ጌታነህ ከበደ ምንም እንኳን ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት ቢኖረዉም በትላንትናው ዕለት የመልቀቂያ ደብዳቤውን ለክለቡ አስገብቶ ተቀባይነትን ማግኘቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም ለደቡብ ፖሊስ ፣ ደደቢት ፣ ለደቡብ አፍሪካዉ ቢድቬስት ዊትስ እንዲሁም ያለፉትን ሶስት አመታት በፈረሰኞቹ ቤት መጫወት የቻለዉ አጥቂዉ ጌታነህ ከበደ ሁለት አመታትን በሚቆይ የኮንትራት ዉል በዛሬዉ ዕለት ለወልቂጤ ከተማ ፊርማውን ማኖሩ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ