በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዉድድር አመት ቅዱስ ጊዮርጊስ የዲሲፕሊን ግድፈት ፈፅመዋል ያላቸዉን አራት ተጫዋቾች ማለትም አስቻለዉ ታመነ ፣ ጋዲሳ መብራቴ ፣ ሙሉአለም መስፍን እና ጌታነህ ከበደ በወርሀ መጋቢት ከክለቡ ማሰናበቱ ይታወሳል። ከክለቡ ከተሰናበቱት ተጫዋቾች መካከልም ተከላካዩ አስቻለዉ ታመነ ወደ ፋሲል ከነማ ፣ የመስመር አጥቂዉ ጋዲሳ መብራቴ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ሙሉአለም መስፍን ወደ ሲዳማ ቡና ማምራታቸዉ ይታወቃል።
ከነርሱ በተጨማሪም አጥቂዉ ጌታነህ ከበደ ምንም እንኳን ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ቢያያዝም እስከ አሁን ድረስ በይፋ የትኛዉንም ክለብ ያልተቀላቀለዉ ሲሆን በዛሬዉ ዕለትም ለክለቡ ያቀረበዉ የመልቀቂያ ወረቀት ተቀባይነት አጊኝቶ ከክለቡ መሰናበቱን የክለቡ ፅህፈት ቤት አስታዉቋል። በዚህ መሰረትም ጌታነህ ከበደ ከመስከረም 18 ቀን 2014 ጀምሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰናበተ ሲሆን በክለቡ ቆይታ ላበረክተው አስተዋጽኦ ክለቡ ምስጋናዉን አቅርቧል።
© Saint George Sa official
አስተያየት ይስጡ