የዝውውር መስኮቱን ከሌሎቹ ክለቦች ዘግይተው የተቀላቀሉት ክትፎዎቹ ሲጠበቅ የነበረውን ግብ ጠባቂ ሲልቭያን ጎቦሆን በይፋ አስፈርመዋል ።
ዕድሜው 32 የሆነው እና ቁመቱ 1 ሜትር ከ91 ሳንቲ ሜትር የሚረዝመው ግብ ጠባቂ ከአፍሪካ ኃያላን ክለቦች አንዱ ለሆነው ቲፒ ማዜምቤ ለ7 አመታት መጫወት ችሏል ።
በተጨማሪም ሲልቪያን ጎቦሆ ለሀገሩ አይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድንም በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ለካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ባህር ዳር ላይ ኢትዮጵያ በሽመልስ በቀለ እና በሱራፌል ዳኛቸው ግቦች አይቮሪኮስትን 2 – 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ የቡድኑ ግብ ጠባቂ ነበር ።
አስተያየት ይስጡ