በዝዉዉሩ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የዉድድር አመቱን በወልቂጤ ከተማ ያሳለፈዉን አማካኙን ፍሬዉ ሰለሞን የግላቸዉ ማድረግ ችለዋል።
በድንቅ ብቃት ረዘም ላለ አመት በመጫወት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነዉ አማካኙ ፍሬዉ ሰለሞን /ጣቁሩ/ በአሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ የሚመራውን ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለ አራተኛው ተጫዋች ሁኗል።
በቀጣዩ የዉድድር አመት ላይ ጠንክረዉ ለመቅረብ ያሰቡት ሲዳማ ቡናዎች የክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ከተጀመረ በኋላ ሁለቱን የመስመር አጥቂዎች ቡሩክ ሙሉጌታ እና አንዋር ዱላን ከኮልፌ ቀራኒዮ እንዲሁም ትናንት ረፋድ ላይ የቀድሞ ተጫዋቹን ሙሉአለም መስፍንን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ማስፈረማቸዉ ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ