መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ሀዋሳ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል!!
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሀዋሳ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል!!

አጋራ
አጋራ

በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የዉድድር አመቱን ያጠናቀቁት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ዘንድሮ ግማሽ አመቱን በአዳማ ከተማ ያሳለፈውን ዘርዐይ ሙሉ በዋና አሰልጣኝነት መቅጠራቸው ተሰምቷል።

በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የተጠበቁትን ያክል መሆን ያልቻሉት ሀዋሳዎች በወጣቱ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እየተመሩ የዉድድር አመቱን 6ኛ ደረጃን በመያዝ በሰንጠረዡ ወገብ ላይ ማጠናቀቅ ችለዉ ነበር።

ባሳለፍነው ሳምንት ሀምሌ 1 ላይ የዝዉዉር መስኮቱ መከፈቱን ተከትሎ ክለቦች ራሳቸዉን ለማጠናከር በስፋት ወደ ገበያዉ የወጡ ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል አንዱ የሆነዉ ክለቡ የቀድሞ አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት ወደ ሀድያ ሆሳዕና መሄዱን ተከትሎ ያለፉትን ቀናት አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ዝግጅት ላይ የነበሩት ሀዋሳዎች አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በሁለት አመት የኮንትራት ጊዜ አስፈርመዋል።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ያለፋትን አመታት በሲዳማ ቡና ቤት ጠንካራ የሚባል ቡድንን መስራት ችሎ የነበረ ሲሆን በዘንድሮው አመት ግን እንደቀድሞው መሆን ሳይችል በመቅረቱ ክለቡ አሰልጣኝ ዘርዓይን ማሰናበቱ ይታወሳል። ከዚያም በኋላ አሰልጣኙ በአዳማ ከተማ ቤት ከአምስት ወራት ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...