የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን በየትኛውም የኘሪሚየር ሊግ ክለብ ከ3 በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማስፈረም እንደማይቻል ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
ቀደም ሲል በነበረው የውጭ ሀገር ተጫዋቾች የዝውውር መመሪያ መሠረት አንድ ክለብ እስከ አምስት ድረስ የውጭ ሀገራት ተጫዋቾች የሚያስፈርምበት አሰራር ከ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ ቁጥሩን በመቀነስ 3 ተጫዋቾች ብቻ ማስፈረም የሚችሉ መሆናቸውን ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት አሳውቋል፡፡
በተጨማሪም በከፍተኛ እና በ1ኛ (በብሔራዊ ሊግ) ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦች ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማስፈረም የማይቻሉ መሆኑን ገልጿል፡፡
አስተያየት ይስጡ