መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “አዳማ ከተማን በውጤት እንታደገዋለን”ታፈሰ ሰርካ /አዳማ ከተማ/
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎች

“አዳማ ከተማን በውጤት እንታደገዋለን”ታፈሰ ሰርካ /አዳማ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ ለደቡብ ፖሊስ፣ ለመከላከያ እና ለመቀለ 70 እንደርታ ቡድኖች ተጫውቶ አሳልፏል። በእዚህ ዓመት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ደግሞ ለአዳማ ከተማ እየተጫወተ ይገኛል።

ይሄ የቀኝ መስመር የተከላካይ ስፍራ ተጨዋችም ታፈሰ ሰርካ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በሐዋሳ ከተማ ነው። ከዚህ እና በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ለአዲሱ ቡድኑ ሁለት የድል ግቦችን ካስቆጠረው ተጨዋች ጋር ሀትሪክ ድረ-ገፅ ያደረገችው ቆይታ ይህንን ይመስላል።

የፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ላይ ምርጥ ጊዜን ስላሳለፈበት ቡድን

“ከሁሉም በበለጠ ለመከላከያ ስጫወት ነው ጥሩ የሚባል ጊዜን ያሳለፍኩት። ቡድናችን ያኔ ጥሩ ስብስብም ነበረው። በእንቅስቃሴ ደረጃም ተመችቶኝ ተጫውቼ ሁለት ጎሎችን እስከማስቆጠር ደረጃም ተጉዤ ነበር። ያ ወቅትም አይረሳኝም”።

በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ ስላዘነበት ጊዜ

“ያዘንኩት ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወተው መከላከያ በወረደበት ወቅት ነው። መከላከያ የሀገሪቱ ምርጥ ቡድን ነበር። መውረድም አልነበረበትም”።

በመቀለ 70 እንደርታ ስለነበረው የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው

“ወደዚህ ቡድን ስመጣ ስኳዱ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ጥሩ ብቃቴን አሳይ ነበር ብዬ ብዘጋጅም ከመሰለፍ እና አለመሰለፍ ጋር ተያይዞ አገባቤ ወጣ ገባ ይል ስለነበርና ብዙም የመጫወት እድልን ስላላገኘው በእዚህ መልኩ ነው ከክለቡ ጋር ላሳልፍ የቻልኩት”።

በአዳማ ከተማ ስላለው የእዚህ ዓመት የሊግ ጅማሬው

“ወደ ቡድኑ ስመጣ ራሴን ለማሳየት በጣም ዝግጁ ነበርኩ። አሰልጣኙም እኔን ሲያናግረኝ በመሀል ተከላካይነት እንድጫወትም ነበር። ያኔም እኔ የቀኝ ተመላላሽ ተጨዋች ነኝ አልኩትና ሳወራው በእዛ ቦታ ላይ አየኝና ሰዎችም ስለ እኔ ጥሩነት ስለነገሩት በምፈልገው ቦታ ላይ መጫወት ጀመርኩ። በእስካሁኑ የቡድኑ ቆይታዬም ጥሩ ጊዜን እያሳለፍኩ ነው”።

ባሳለፈው የኳስ ቆይታው ምርጥ ጥምረቱ

“በመከላከያ ስጫወት ከአዲስ ተስፋዬ ጋር የነበረኝ ነው። ያ ጥምረታችንም መቼም የማይረሳኝ ነው”።

ስላሳለፈው የኳስ ህይወት

“ሁሌም ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም እግር ኳስን በጣም እወደዋለሁና”።

በእግር ኳሱ ማሻሻል የሚፈልገው

“በፊት በምጫወትበት ቦታ ወደፊት ብዙ የመሄድ አቅም የለኝም ነበር። መከላከሉ ላይ ስለማተኩርም ቆሜም ነበር የምጫወተው። አሁን ግን እየተከላከልኩም ስለማጠቃ ብዙ ነገሮችን አሻሽያለሁ።

የልጅነት ዕድሜው ተምሳሌቱ

“እሱ የኮረም ሰፈር ልጅ እና የሐዋሳ ከነማ ተጨዋች ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይኖር ነበር። በድሉ ይባላል። አድንቄ ያደግኩት እሱን ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ እነ አዳነ ግርማን ሽመልስ በቀለና በሀይሉ አሰፋን ሳይ ደግሞ ለኳሱ ያለኝ ፍቅር የበለጠ ጨመረና እነሱንም አደነቅኩኝ”።

የአዳማ ከተማ የሊግ ጉዞና ዘንድሮ ምን ውጤትን እንደሚያስመዘግብ

“አዳማ ትልቅ ቡድን ቢሆንም እስካሁን እያስመዘገበ ያለው ውጤት የሚመጥነው አይደለም። በሊጉ ቆይታም በሚፈልገው መልኩ ስኬትን እንዳያስመዘግብ ያደረገው የዝግጅት ጊዜውን ዘግይቶ ስለጀመረ ነው። ከዚህ በኋላ ግን ቡድናችን ባሉት ክፍተቶች ላይ የሚጨምራቸው ልጆች ስለሚኖሩና ቡድኑም የበለጠ እየተዋሀደ ስለሚመጣ ቡድኑን በውጤት ደረጃ ከምንም ነገር እንታደገዋለን”።

በቤተሰባቸው ውስጥ ብቸኛው ስፖርተኛ እሱ እንደሆነ

“በእኛ ቤተሰብ ውስጥ 3 ወንድም እና 4 እህቶች አሉኝ። አንዱ ወንድሜም በፕሮጀክት ደረጃ ከእነ ፍሬው ሰለሞን ጣቁሩ ጋር ይጫወት ነበር። በአሁን ሰዓት ላይ ግን ብቸኛው ስፖርተኛ እኔ ነኝ”።

የእግር ኳስን መጫወት ሲጀምር በቤተሰቡ ዘንድ ተፅህኖ ኖሮበት እንደሆነ

“በፍፁም ተፅህኖ አልነበረብኝም። በተለይ ደግሞ እህቴ በፕሮጀክት ደረጃ የሚጫወተውን ወንድሜ ያኔ እየተመለከተች ለምን ኳስን አትጫወትም ትለኝ ነበር። ሌሎቹም ኳስን እየተጫወትኩ እንድማርም ይፈልጉ ነበር”።
በእግር ኳሱ ለማን ቡድን መጫወትን ያልም እንደነበር
“ያኔ ለመከላከያ እና ለኢትዮጵያ ቡና ነበር መጫወትን እፈልግ የነበረው። የመከላከያ ምኞቴ ተሳክቷል። በቀጣይነት ደግሞ ጠንክሬ ከሰራው ለኢትዮጵያ ቡናም ሆነ ለሌሎች ትላልቅ ቡድኖች መጫወቴ የማይቀር ይሆናል”።

በመጨረሻ

“በእግር ኳሱ ትልቅ ደረጃ የመድረስ እልም አለኝ። ለዛም ገና ወጣት ስለሆንኩ ጠንክሬም እየሰራው ነው። ይህን ካልኩ ለእስካሁኑ ለደረስኩበት ደረጃ በብዙ ነገር ለረዱኝ ፈጣሪዬ፣ ቤተሰቦቼ፣ እንደ አባትና እናት ሆኖ በፕሮጀክት ደረጃ ላሰለጠነኝ እና ከቤት ጭምር እየጠራ ይመክረኝ ለነበረው ያሬድ ገመቹና ስማቸውን ላልጠራዋቸው ሁሉ ምስጋና አለኝ”።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...