መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ የተቋረጠው የወልዋሎ አዲግራትና የመቐለ ከተማ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ ተወሰነ
መቐለ ከተማወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የተቋረጠው የወልዋሎ አዲግራትና የመቐለ ከተማ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ ተወሰነ

አጋራ
አጋራ

በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት የተቋረጠው የወልዋሎ አዲግራት እና መቐለ ከተማ የሁለተኛ አጋማሽ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲደረግ ተወሰነ።

በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 17 ሳምንት የትግራይ ደርቢ ጨዋታ በወልዋሎ አዲግራት 1-0 መሪነት እየተመራ ወደ መልበሻ ክፍል ያመራው ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ላይ በሁለቱ የክለብ ደጋፊዎች በተነሳ ረብሻ ለመቋረጥ መገደዱ እሚታወስ ነው። በማግስቱ አርብ 4:30 ጨዋታው ከተቋረጠበት እንደሚቀጥል ተገልፆ የነበረ ፣ ሲሆን ጨዋታው በደጋፊ ታጅቦ ይካሄዳል ፣ አይካሄድም በሚል ምክንያት የሁለቱ ክለብ ሀላፊዎች ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ሳይካሄድ ቀርቷል።

በቀጣይ ቡድኖቹ ቀሪውን 45 ደቂቃ እንዲጫወቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሁለቱም ቡድኖች በገለልተኛ ሜዳ ጨዋታቸው እንዲያካሂዱ የአዲስአበባ ስታዲየምና የአክሱም ስታዲዮም በምርጫነት ማቅረቡ ታውቋል። የተቋረጠው ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ቀን አልተቆረጠለትም ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...