የተቋረጠው የትግራይ ደርቢ የውልዋሎ አዲግራት እና የመቐለ ከተማ ጨዋታ መች እንደማካሄድ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በሰሜን ደርቢ ወልዋሎ አዲግራት ከ መቐለ ከተማ ዛሬ የተከናወነው ጨዋታ ባለሜዳው ቡድን ወልዋሎ አዲግራት በ33ኛው ደቂቃ አሳሪ አልማህዲ ባስቆጠራት ጎል 1-0 እየመራ የመጀመሪያው አጋማሽ እንደተጠናቀቀ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች መሐከል በተፈጠረው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ጨዋታው ሁለተኛው አጋማሽ ሳይከናወን መቋረጡ ይታወሳል፡፡ ይኽንን ተከትሎ ምሽት ላይ በሥራ አስፈፃሚው አማካኝነት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ የጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ነገ (ዓርብ) ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በሌሉበት ያለተመልካች የሚከናወን ይሆናል፡፡

አስተያየት ይስጡ