መነሻ ገጽ ዜናዎች ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲ ተጨዋቾችን በመቀነስና በማምጣት ቅድመ ዝግጅታቸውን  አጠናክረው ቀጥለዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲ ተጨዋቾችን በመቀነስና በማምጣት ቅድመ ዝግጅታቸውን  አጠናክረው ቀጥለዋል

አጋራ
አጋራ

ወልዋሎ  አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዙር የሊግ ጨዋታ ተጠናክረው ለመቅረብ  በአዲሱ አሰልጣኝ ፀጋየ ኪዳነማርያም እየተመሩ  በቀን 2 ጊዜ ቅድመ ዝግጅታቸውን እየሰሩ ነው፡፡
በሊጉ መጀመሪያ ሳምንታት ክስተት የነበሩት ወልዋሎ  አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች የሊጉ የመጀመሪያው ዙር አጋማሽ ጀምሮ ከሳምንት ሳምንት በውጤት ማጣት ቀውስ በመግባታቸው አሰልጣኝ እስከ መቀየር የደረሰ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የኘሪሚዬር ሊግ 15 ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ8 የግብ ዕዳ በደረጃ ሰንጠረዡ በ12ኛነት የተቀመጡት ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲዎች በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ተስፋ ያልተጣለባቸውን ተጨዋቾችን በመልቀቅ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ እያመጡ ከመሆኑም ባሻገር በቀን 2 ጊዜ ልምምዳቸውን አጠናክረው እየሰሩ ነው፡፡

የቢጫ ሰርጓጆቹ አዲሱ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም 3 አዲስ ተጨዋቾችን ፡ማናዬ ፋንቱን ከኢትዮጵያ ቡና፡አለምነህ ግርማ/ሶራ/ ከመቆለ ከተማ እና ታዲዬስ/ፔሌ/ን ከአርባ ምንጭ ከተማ ሲያስፈርሙ፡፡ 4 ነባር  ተጨዋቾችን ብሩክ አየለ ፡ቢኒያም አየለ ፡በለጠ ግብ ጠባቂውን እንዲሁም  እዬብ  ወ/ማርያምን ከስብስባቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲቀንሱ ሌሎች ተጨዋቾችንም የመቀነስ ዕቅድ እንዳላቸው አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ገልፀዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...