መነሻ ገጽ ዜናዎች የዝውውር ዜና ፋሲል ከተማ ኬኒያዊውን ሁለገብ ተጨዋች ሰንደይ ሙቱኩን አስፈረመ
ዜናዎችየዝውውር ዜናዎችፋሲል ከተማ

የዝውውር ዜና ፋሲል ከተማ ኬኒያዊውን ሁለገብ ተጨዋች ሰንደይ ሙቱኩን አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

ፋሲል ከተማ ኬኒያያዊውን የመሃል ተከላካይ ሰንደይ ሙቱኩን በ1 አመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡
ሰንደይ ምትኩ በመሃል ተከላካይና አማካኝ ስፍራ  የሚጫዎት ሁለገብ ተጨዋች ሲሆን በትውልድ ሀገሩ ኬኒያ በ3ኛ ዲቪዚዬን የሚሳተፈውን ያታ ኮምቦይን እግር ኳስ ክለብ በ2015 እ,ኤ,አ የተቀላቀለ ሲሆን በቆይታው የተጨዋቹን የኳስ ክህሎትና ብስለት የተመለከቱት በ2ኛ ዲቪዚዬን የሚሳተፉት ካካሜጋ ሆምቦይዝ ክለብ በአመቱ መጨረሻ  ወደ ክለባቸው አዛወሩት፡፡

ተጨዋቾቹ በ2ኛ ዲቪዚዬን በሚሳተፈው ካካሜጋ ሆምቦይን እግር ኳስ  ክለብ  በነበረው ቆይታ የክለቡ አምበል ሆኖ  የተጫወተ ሲሆን ባሳለፍነው አመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለሲዳማ ቡና በመፈረም ከክለቡ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ የሚታወስ ቢሆንም በአመቱ መጨረሻ ባሳለፍነው የክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን ለቆ ድሬድዋ ከተማን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው፡፡

ሰንደይ ሙቱኩ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ6 ወር ቆይታ  የተጠበቀውን ያህል እንቅስቃሴ ሳያደርግ ትናንት በስምምነት ከክለቡ ጋር የነበረውን ኮንትራት ውል በማፍረስ ዛሬ ለፋሲል ከተማ በ1አመት ኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡
የፋሲል ከተማ የክለቡ አመራሮች የአጥቂ ክፍሉን  ለማጠናከር በዝውውሩ ላይ ተጠናክረው እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...