መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ሲሸነፍ ደደቢት አሁንም በማሸነፍ ግስጋሴው ቀጥሏል።
ሪፖርትኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢት

ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ሲሸነፍ ደደቢት አሁንም በማሸነፍ ግስጋሴው ቀጥሏል።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት 1ጨዋታ አ/አ ላይ ሲደረግ ደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው ደደቢት ጌታነህ ከበደ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፎ መውጣት ችሏል።
10:16 ሲል የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በብዙ ደጋፊዎች ታጅቦ የተጀመረ ነበር። በጨዋታው ደደቢት4-3-3 ኢት.ቡና በአንፃሩ 4-1-4-1 የጨዋታ ዘይቤን ይዘው ወደሜዳ ገብተዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከጅምሩ ተመጣጣኝ ፉክክር የታየበት ሲሆን ቶሎ ቶሎ ወደግብ ለመድረስ ግን ብዙ የታዩ ጥረቶች አለነበሩም።
12ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው ኤሊያስ ማሞ አሰራት መገርሳን አታሎ ለአክሊሉ ያሳለፈለትን ኳስ ለአክሊሉ ወደ ግብ ሞክሮት የደደቢቱ ግብ ጠባቂ ክሌመንት አወጥቷታል። 26ኛው ደቂቃ ላይ ከኢትዮጵያ ቡና በኩል በጥሩ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ የዋለው እያሱ ታምሩ ለዮሐንስ ያሻገረለትን ኳስ ግብ ጠባቂው ክሌመንት አውጥቶታል። በተደጋጋሚ ወደ ደደቢት የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ያገኙአቸውን የግብ ማግባት አጋጣሚዎች ሳይጠቀሙባቸው ቀርተው ግብ ሳያስቆጥሩ ለመውጣት ተገደዋል። 34ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ ከ16.50 ውጪ የሞከራት ኳስ ለጥቂት በግብ አናት ላይ ወጥቷል፡፡ 45ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከበደ በግራ በኩል ከኢትዮጵያ ቡና የፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ ያገኛትን ኳስ በግሩም ሆኔታ ከመረብ በማሳረፍ 1-0 በመመምራት ለእረፍት እንዲወጡ አስችሏቸዋል፡፡

ከእረፍት መልስ ኢት ቡና ውጤቱን ለመቀልበስ በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ጫና ሲያደርጉ ደደቢት በአንፃሩ ውጤቱን አስጠብቆ ለመውጣት አፈግፍጎ አጋጣሚ ሲገኝ በመልሶ ማጥቃት በመጫወት ጨዋታውን ጨርሷል። 64ኛው ደቂቃ ላይ አቤል ያለው ከኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ሀሪስተን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው የሞከራትን ኳስ ሀሪስተን አውጥቷታል። 74ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳኑሚ እንዲሁም 78ኛው ደቂቃ ላይ አስቻለው ግርማ ከግብ ጠባቂው ክሌመንት ጋር ተገናኝተው የወጣባቸው ኳሶች እጅግ የሚያስቆጩ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ በዚህ ጨዋታም ሳሙኤል ሳኑሚ እጅግ የሚያስቆጩ እና አልፎ አልፎም ኢላማቸውን ያልጠበቁ ኳሶችን ሲያባክን ውሏል።

77 ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው አቤል ማሞ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ ውጪ የሞከራትን ኳስ በዕለቱ ድንቅ ሆኖ የዋለው ክሌመንት አዞንቶ በድንቅ ሁኔታ አድኗታል፡፡ ከዚህም በኋላ ይሄ ነው የሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴ ሳይደረግበት ጨዋታው በደደቢት 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ውጤቱንም ተከትሎ ደደቢት 19ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ ጅማ አባጅፋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 5አድርሶ መሪነቱን ሲያጠናክር ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ ከመሪው ደደቢት በ8 ነጥቦች ርቆ 11ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የአሰልጣኞች አስተያየት

የደደቢቱ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ
“እንደማንኛውም ክለብ ተዘጋጅተን ነው የምንመጣው ክብደቱ አልታየንም። ሰሞኑን እያሳዩት ባለው አቋም የተሻለ ነገር እንፈጥራለን ብለን ነበር የገባነው፤ እንደፈለግነውም 3ነጥብ አግኝተናል። በጣም ደስ ብሎኛል።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ጥንካሬያቹ ምንድነው ተብለው ለተጠየቁት አሰልጣኙ ሲመልሱ “ዋናው ጥንካሬያችን ወጣቶችን ልምድ ካላቸው ጋር አቀናጅተን መስራታችን እና ለስራችን ትኩረት ሰጥተን መስራታቸን ነው። ስንገባ ፈጣን የማጥቃት እቅድ ይዘን ነበር የገባነው፤ ነገር ግን ትንሽ መደናገሮች ነበሩ። በሁለተኛው አጋማሽ ግንተረጋግተን በመጫወት የምንፈልገውን ነገር አሳክተናል። በልጆቼም እጅግ በጣም ኮርቻለሁ።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ
“በዛሬው ጨዋታ በሚገባ ተጫውተናል፤ ኳስ በማንሸራሸር ቡና የሚታወቅበትን ጨዋታ ለመጫወት ሞክረናል። ብዙ ግብ የማግባት አጋጣሚዎችን መፍጠር ችለናል ነገር ግን እጅግ በጣም ጠንካራ ግብ ጠባቂ ነው የገጠመን። ሁሉንም ደጋፊዎች ላሳዩን ድንቅ ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ፤ ሁሌም ከጎናችን እንዲሆኑ እንፈልጋለን። ከሽንፈቱ ባሻገር በልጆቼ በጣም ኮርቻለሁ፤ በቅርቡ ኢትዮጵያ ቡና ወደ ጥንካሬው ይመለሳል።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...