መነሻ ገጽ አርባምንጭ ከተማ ​ስንብት | አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያምን  አሰናበተ
አርባምንጭ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​ስንብት | አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያምን  አሰናበተ

አጋራ
አጋራ

አርባምንጭ ከተማ እና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማሪያም የመለያየታቸው ነገር እርግጥ ሆኗል፡፡
አሰልጣኙ ከክለቡ  እንዲሰናበቱ እንደ ምክኒያት የቀረበው በ2010 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ባስመዘገቡት ውጤት ሲሆን በ8ጨዋታዎች  4ተሸነፈው 3አቻ በመውጣት አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፉ ሲሆን በ6ነጥብ  በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ 14ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጡ በመቻላቸው ነው፡፡ አሰልጣኙ  በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ 6 ተጫዋቾችን ቢያስፈርሙም ያስመዘገቡት ውጤት የክለቡን የቦርድ አካላትና የቡድኑን ደጋፊዎች ያላስደሰተ መሆኑ  እንደምክኒያት ተጠቅሷል፡፡
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ስለ ጉዳዮ ከድህረ ገፃችን ጋር ባደረጉት ቆይታ

ክለቡ ለተጫዋቾች እና ለአሰልጣኞች  ደሞዝ ፤ ትጥቅ ፤ እና የምግብ አገለግሎት በተገቢ ሆኔታ ሊያቀርብ አልቻለም ፡፡ ያለበትን ጉድለቶች እንዲያሟላ በተደጋጋሚ ስጠይቅ ቆይቻለሁ፡፡ ቦርዱ ይህን ሳያሟላ ወጤት መፈለጉ እያስገረመኝ ነው፡፡

ከቡድኑ ጋር ብለያይም  አዲስ ነገር አይደለም የትም ሄጄ ማሰልጠን እችላለሁ በአጭር ቀናት ውስጥ አዲስ ክለብ እንደምይዝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ነገ ወደ አዲስአበባ እመለሳለሁ ፡፡ ክለቡ ላደረገልኝ ነገር አመሰግናለሁ ፡፡አሁን የተፈጠረው ነገር  ለኔ ትምህርት ሆኖኛል፡፡ “በማለት ለድህረገፃችን አስተያየታቸውን አጠቃለዋል

የአርባምንጭ ከተማ ኘሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ጊሌ በበኩላቸው “አሰልጣኙ እንደሚጠቅመን እናውቃለን ነገር ውጤት እና ውጤትን ተንተርሰን፡አሰልጣኙን ልናሰናብት ተገደናል፡፡ በሄደበት ሁሉ መልካሙን እንመኝለታለን” በማለት አስተያየታቸውን ለድህረ-ገጻችን ተናግረዋል ፡፡

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ከዚህ በፊት ትራንስ ኢትዮጵያን ፤ ሀረር ከተማን ፤ኢትዮጵያ ቡናን ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ፤ ማሰልጠናቸው እሚታወስ ነው

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...