መነሻ ገጽ CYCLE ኤርትራ የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነች
CYCLEኤርትራዜናዎች

ኤርትራ የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነች

አጋራ
አጋራ

በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው 14ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በኤርትራ አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ተጠናቀቀ።

ከመጋቢት 5/ 2011ዓ.ም. ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው በዚሁ ውድድር 13 የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፈዋል፡፡

በዚህም  የኤርትራ ብስክሌት ቡድን በሰባት የወርቅ፣በስድስት  የብር እና በአራት ነሐስ ሜዲሊያዎች አንደኛ  ሆኖ አጠናቋል፡፡

ኢትዮጵያ ደግሞ ሰባት የወርቅ፣ አምስት የብር እና ሁለት የነሐስ  ሜዲሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃላች፡፡

የሩዋንዳ ብስክሌት ቡድን በበኩሉ ሁለት የወርቅ እና ሶስት የነሐስ   ሜዲሊያዎችን በመሰብሰብ ሶስተኛ ወጥቷል፡፡

በኤርትራ አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ሲጠናቀቅ

መኽሰብ ደበሳይ- — ወርቅ
️ ሞሳና ደበሳይ — —ወርቅ
️ ሄኖክ ሙሉብርሃን- –ወርቅ
ደሴት ኪዳነ— —-ወርቅ

በኤርትራ ብስክሌት ቡድን አጠቃላይ አሸናፊነት  ተጠናቋል::

ደቡብ አፍሪካ በድምሩ አራት ፣  አልጀሪያ እና   ቡርኪናፋሶ እያንዳንዳቸው ሁለት  ሜዳሊያዎች በማግኘት ደረጃ ውስጥ መግባት እንደቻሉ ታውቋል፡፡

የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርዕስቱ ይርዳው በመዝጊያ ስነስርዓት ወቅት እንዳሉት የብስክሌት ውድድሩ እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ክልል ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ማስተናገድ እንደሚቻል የተረጋገጠበት ነው፡፡

በዚህ ውድድር ከትግራይ ክልል የመጡ ተሳታፊዎች የተሻለ ውጤት ማስገኘት እንደቻሉ ጠቅሰው ሌሎች ክልሎችም በዘርፉ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል፡፡

የአማራ ክልል ስፖርት ከሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዘዘው ጫኔ በበኩላቸው የክልሉ የፀጥታ ኃይል፡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ማህበረሰቡ ባደረገው ጠንካራ ህብረት ውድድሩ በሰላም  መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴረሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ገዳ በበኩላቸው በውድድሩ ጠንካራ እንደነበር ገልፀው የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ፡

ከሀገራቱ ከ100 በላይ ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና  ውድድር ሲጠናቀቅ ለአሸናፊዎቹ የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...