ኡጋንዳዊው ኢንተርናሽናል ክሪዚስቶም ንታንቢ በ2009 ዓ.ም ከጅማ አባቡና ጋር መልካም እንቅስቃሴን ማድረጉን ተከትሎ ለአዳማ ከተማ ና ለኢትዮጵያ ቡና በመፈረሙ ሁለቱን ክለቦች አወዛግቦ በመጨረሻም የኢትዮጵያ እግር ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ቡና እንዲጫወት በመወሰኑ ለሁለት አመት ኢት.ቡና መፈረሙ እሚታወስ ነው ፡፡
ከዚህ ተጫዋች ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በተደረጉ 10 ጨዋታዎች መሠለፍ የቻለው 2ጨዋታዎች ብቻ እንደነበር እሚታወቅ ሲሆን ጉዳቱ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የጉዳቱን ሀሰተኛነት በM.R.I ምርመራ በማረጋገጥ ተጫዋቹ ያለተጫወተበትን ጨዋታዎች ገንዘብ እንዲመልስ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ በደብዳቤው አስታውቋል፡፡
የደብዳቤው መሉ ይዘት ይሄን ይመስላል፡፡
- ማሰታውቂያ -
“ክሪዚስቶን ንታንቢን ይመለከታል
የክለባችን የተከላካይ አማካይ በመሆን እየተጫወተ የሚገኘው ክሪዚስቶን ንታንቢ ለ2010ዓ.ም የወንዶች የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከጅማ አባጅፋር ወደ ክለባችን እንደተዘዋወረ ይታወቃል፡፡ ይህ ተጫዎች ለቡድኑ ውጤት ከፍተኛ አስተዋእጾ እንደሚያበረክት ታምኖበት በዘንድሮ ዓመት ቡድናችንን በወር ያልተጣራ በ120,769.23 (አንድ መቶ ሀያ ሺ ሰባት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር) ፈርሞ ተቀላቅሎ ነበር፡፡
ይህ ተጫዎች ውድድሩ ከጀመረ አስር ጨዋታዎች መካከል መሰለፍ የቻለው በሁለት ጨዋታዎች ብቻ ሲሆን በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ጉዳት ላይ እንደሆነ በተደጋጋሚ በመግለጽ እና የሀኪም ማስረጃዎች በማቅረብ ሳይሰለፍ ቀርቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ያሳሰበው ክለባችን ባደረገው የ ኤም አር አይ ምርመራ ተጨዋቹ ምንም አይነት ጉዳት ያልነበረበትና የሌለበት መሆኑን አረጋግጧል፡፡
“በመሆኑም በዛሬው እለት ለተጫዎቹ ክለባችን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የሰጠ ሲሆን በደብዳቤው ላይም ያደረገውን ስህተት በዝርዝር በመግለጽ ያልሰራበትን ገንዘብ እንዲመልስ ተጠይቋል፡፡ ጉዳዩንም በግልባጭ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡
በቀጣይ ያለውን ዝርዝር ጉዳይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡
ምንግዜም ኢትዮጵያ ቡና”