መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍፃሜውን ባገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊርጊስ ዋንጫ ሲያነሳ 3 ክለቦች ሊጉን ተሰናብተዋል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ፍፃሜውን ባገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊርጊስ ዋንጫ ሲያነሳ 3 ክለቦች ሊጉን ተሰናብተዋል

አጋራ
አጋራ

 


የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንትዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።

የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት የመጨረሻ የሊጉ ጨዋታዎች ዛሬ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተካሂደዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደ ጨዋታም ሻምፒዮናነቱን ቀድሞ ያረጋገጠውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አገናኝቷል።

ጨዋታምውም በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊተን የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎም ንግድ ባንክ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።

ወላይታ ድቻ ከደደቢት ያደረጉት ጨዋታ በወላይታ ድቻ 4ለ2 አሸናፊነት የተጠናቀቀሲሆን፥ ድሬ ደዋ ከተማ ከጅማ አባ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በድሬደዋ ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ይህንን ውጤት ተከትሎም ጅማ አባ ቡና ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።

ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ፤ ኢትዮጵያ ቡና ከአርባ ምንጭ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በሜዳው ፋሲል ከነማን ያስተናገደው አዳማ ከተማ ፋሲልን 2ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፤ ወልዲያ ላይ አዲስ አበባ ከተማን ያስተናደው ወልዲያ ከተማ ጨዋታውን 1ለ0 አሸንፏል።

የጨዋታውን ውጤት ተከልተሎም አዲስ አበባ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደ ሶስተኛ ክለብ ሆኗል።

ሲዳማ ቡና ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታም 1ለ1 በሆነ አቻው ውጤት ተጠናቋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በድምሩ በ62 ነጥብ በመያዝ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን 1ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ ደደቢት እና አዳማ ከተማ በእኩል 51 ነጥብ በግብ ተበላልጠው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልዲያ ከተማ እና መከላከያ ከ4ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደራጃ በመያዝ ፕሪምየር ሊጉን አጠናቀዋል።

ላለመውረድ ከፍተኛ ትንንቅ በነበረበት ወራጅ ቀጠናውስ የነበሩት ጅማ አባ ቡና፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ደረጃ ያለውን በመያዝ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዳቸው ተረጋግጧል።

የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢነቱ ጌታነህ ከበደ 25 ጎሎችን በማስገባት በአንደኝነት አጠናቋል።

በዚህም መሰረት ጌታነህ ከበደ ለረጅም ጊዜ በዮርዳኖስ አባይ እጅ የነበረውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረ ወሰንን በእጁ ማስገባት ችሏል።


ሻምፒዮን መሆናቸውን  ቀድመው ያረጋገጡት ፈረሰኞቹ ደስታቸውን ሲያከብሩ…..


Photo source-የፈረሰኞቹ ገጽ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...