መነሻ ገጽ ሪፖርት ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን በሰፊ ጎል ረምርሟል
ሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማፋሲል ከተማ

ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን በሰፊ ጎል ረምርሟል

አጋራ
አጋራ

በ2ተኛው ሳምንት ቅዳሜ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ድሬድዋ ከተማን አስተናግዶ በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል።ፋሲል ከነማ ወደ አዳማ ተጉዞ 0-0 ካጠናቀቀው ቡድን ኦሲ ማውሊን በ ኢዙካን ቀይሮ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት።

የፋሲል ከነማ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ በ4-5-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት አጼዎቹ በተሻለ መልኩ ተንቀሳቅሰዋ ጨዋታው ገና እንደተጀመረ በሙከራ የታጀበ ነበር። 9ነኛው ደቂቃ ላይ ያሬድ ባየ በረጅሙ ያሻገረለትን ኳስ ሙጅብ ቃሲም በሚገባ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ተከላካዮችን አታሎ ይዞት በመግባት ወደ ግብነት ቀይሮታል።የመጀመሪያ አጋማሽም በፋሲል መሪነት ተጠናቁዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ፋሲል ከነማ ተጫዋቾችን በመቀየር በመጀመሪያው አጋማሽ ተወስዶበት የነበረውን ብልጫ ለመመለስ እና ተጭነው ለመጫወት ሞክረዋል፡፡ሽመልስ ጉግሳ 60ኛው ዕና 73ኛው ደቂቃ አከታትሎ በማግባት የፋሲል ከነማን መሪነት ወደ 3ለ0 አሳድጎታል።ከጎሉ መቆጠር በሁዋላ ፋሲል ከነማዎች ይበልጡን ተጭነው በመጫወት ተጨማሪ ጎል ለማስቆጠር ሙከራ አድርገዋል ሙከራቸውም ተሳክቶላቸው በ 82ኛው ዕና 88ኛው ደቂቃ ሙጅብ ቃሲም አከታትሎ በማግባት ለዕራሱ ሶስተኛውን ለ ፋሲል ከነማ ደግሞ አምስተኛውን በማስቆጠር ጭዋታው ተጠናቁዋል።

ጭዋታው ፍጹም ጭዋነት የተሞላበት ጭዋታ ነበር፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 4 አሳድጉዋል፡፡

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...