መነሻ ገጽ ሪፖርት ​ፋሲል ከተማ፤አዳማ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሜዳቸው ውጪ  ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ማሳካት ችለዋል፡፡
ሪፖርትአርባምንጭ ከተማኢትዮ-ኤሌክትሪክወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

​ፋሲል ከተማ፤አዳማ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሜዳቸው ውጪ  ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ማሳካት ችለዋል፡፡

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር መሰረት ወደ አርባምንጭ ያመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ 3 ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል፡፡ በ13 ደቂቃ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው አልሀሰን ካሉሻ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ቀዳሚ ማድረግ ሲችል፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሲል ላኪ ሳኒ አዞዎቹን በአቻ ውጤት ለእረፍት እንዲወጡ አስችሏል፡፡ ከእረፍት መልስ ተጨነው መጫወት የቻሉት አዞዎቹ በገብረሚካኤል ያእቆብ፤በላኪ ሳኒ ጎል የማግባት ሙከራዎች ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ በ54ኛ ደቂቃ በሲቲ ካፕ ውድድር ጥሩ ግልጋሎት ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ እየሰጠ እሚገኘው ዲዲየር ሊብሬ ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡ በዚሁ የ2-1 ውጤት አዞዎቹ በሜዳቸው ሽንፈትን ሊያስተናግዱ ችለዋል፡፡

——————————————————————

ሌላው በተመሳሳይ ሰዓት የተደረገው በሶዶ ስታዲየም አዳማ ከተማ ን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በሜዳው የ2-1 ሽንፈትን ሊያስተናግድ ችሏል፡፡

በሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጨዋታ በሜዳቸው ከደደቢት ጋር ነጥብ ተጋርተው የወጡት አዳማ ከተማዎች:: በመሀል  ክፍል ተጫዋቻቸው ከነዓን ማርክነህ ሁለት ወሳኝ ጎሎች ሶስት ነጥብ ይዘው መመለስ ሲችሉ፡፡ለወላይታ ድቻ ቡዱኑን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል በ52ኛ ደቂቃ ላይ ጃኮ አራፋት ማስቆጠር ችሏል፡፡


——————————————————————

እንዲሁም ፋሲል ከተማ ወደ ጅማ አጅፋር አምርቶ ነጥቡን አሳክቶ መመለስ ሲችል፡፡

ለፋሲል ከተማ በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ለሁለተኛ ግዜ በመመጣት ለአፄዎቹ የፈረመው ፍሊኘ ዳውዚ ባስቆጠራት ግብ አፄዎቹ ወሳኝዋን ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል፡፡

—————————————————————–

የደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ሪፖርት ሊንኩን ይጫኑ

http://wp.me/p7SLd5-2p8

——————————————————————

የቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ ከተማ የጨዋታ ሪፖርት ሊንኩን ይጫኑ

http://wp.me/p7SLd5-2pd

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...