ጅማ አባ ጅፋር ከሄኖክ ገምቴሳ ጋር ተለያየ

 

የጅማ አባጅፋሩ የተከላካይ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሄኖክ ገምቴሳ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

2010 ክረምት ላይ ፋሲል ከነማ ከለቀቀ በኃላ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀለው ተጫዋቹ አምና በክለቡ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው በተወሰነ መልኩ ክለቡን ያገለገለ ሲሆን ዘንድሮ በአብዛኛው ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውተዋል፡፡ ቀሪ የውል ጊዜ የሚቀረው ተጫዋቹ ለክለቡ ባስገባው የልቀቁኝ ጥያቄ መሠረት ሊለያይ ችሏል፡፡ ሄኖክ ገምቴሳ አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ መጫወቱ የሚታወስ ነው።

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ለሁለተኛው ዙር የፕሪምየር ሊጉ ጉዞ ከተወሰኑ ተጫዋቾች ጋር ሊለያይ እንደሚችል። ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer