ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ላለፉት አንድ አመታት ድሬዳዋ ከተማን በአሰልጣኝነት የመራው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለድሬዳዋ ከተማ ባስገባው የመልቀቂያ ደብዳቤ በስምምነት ከቡድኑ ጋር ሊለያይ ችልዋል፡፡
ሁለቱም አካላት ከድህረ-ገፃችን ጋር አጭር ቆይታ አድርገው የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
አቶ እስከዳር መብራቱ የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ
“እንደማንኛውም ክለብ ቡድናችን ውጤት ይፈልጋል ለዛም ነው ለውጤታማነት ስንል በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከውጪ አውጥተን አመጣን ነገር ግን ክለቡ የተሻለ ደረጃ ላይ አልተገኘም ያም በመሆኑ ምክንያት በቀጣይ ለተሻለ ውጤት አሰልጣኙን እንደ ምክንያት በዋናነት ተጠያቂ በማድረግ ባስገቡት መልቀቂያ መሰረት እንድንለያይ ወስነን ተለያይተናል፡፡”
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው
“የውጤት መጥፋት ያጋጥማል ይህንን በፀጋ ተቀብያለሁ ብቀጥል የተሻለ ደረጃ ላይ ክለቡን ማድረስ አይከብደኝም ነገር ግን የደጋፊዎች ጫና በነፃነት እንዳልሰራ አድርጎኛል፡፡ ለዛም ነው አስቀድሜ መልቀቅ በመፈለጌ በስምምነት ተለያይቻለሁ ለነበረኝ ቆይታም ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡”
አሰልጣኙ ቀጣይ ማረፊያቸው የት ይሆናል እሚለው አየተጠበቅ ሲሆን ሰሞኑን ዋና አልጣኛቸውን ካሰናበቱት ክለቦች መካከል ወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ ጋር እየተያያዘ ይገኛል፡፡

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በአሰልጣኝነት ደቡብ ፖሊስን፤አዳማ ከተማን፤የደደቢት ምክትል አሰልጣኝ ፤ ሀዋሳ ከተማ ፤ሲዳማ ቡናን፤ ድሬዳዋ ከተማን ማሰልጠን ችለዋል፡፡
አስተያየት ይስጡ