“የፋሲል ከነማ አመራሮች የገቡትን ቃል ስላላከበሩ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት ችያለሁ” ሽመክት ጉግሳ

 

በ2011 ዓ.ም ደደቢትን በመልቀቅ ፋሲል ከነማን መቀላቀል የቻለው ድንቁ ሁለገቡ አማካይ ተጫዋቾች ሽመክት ጉግሳ ከሳምንታት በፊት በፋሲል ከነማ ቤት ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ተጫዋቾች በዛሬው እለት ለትውልድ ከተማው እንዲሁም ወላይታ ድቻ በታችኛው ሊግ እያለ ላገለገለው የቀድሞ ቡድኑ ዳግም መቀላቀሉ ታውቋል። ተጫዋቾቹ ከፋሲል ከነማ ጋር ውል እያለው ውሉን አፍርሶ ወደ ወላይታ ድቻ የሄደበትን ምክንያት በተመለከተ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል ተከታተሉን።

ከፋሲል ከነማ ጋር አዲስ የሁለት ዓመት ስምምነት እያልክ እንዴት ወደ ወላይታ ድቻ ሄድክ?

” በመጀመሪያ ፋሲል ከነማ ጋር ውል ለማራዘም በተጠራው ሰዓት ክለቡን እና ደጋፊዎችን አክብሬ ውሌን አራዝሚያለሁ። ሆኖም የክለቡ አመራሮች የገቡትን ቃል ስላላከበሩ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት ችያለሁ”

ከፋሲል ከነማ አመራሮች ጋር በቅርበት አልተነጋገራችሁም ?

“ከክለቡ አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ ለመነጋገር ችያለሁ የዛሬ 15 ቀን የገቡት ቃል እንፈፅማለን ቢሉኝም ቃለ የገቡትን መፈፀም አልቻሉም ለሌሎች ለቡዱን ተጫዋቾች ያደረጉትን ለኔ መፈፀም አለመቻላቸው አስከፍቶኛል። በዚህ አጋጣሚ ለፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ “

ሽመክት ጉግሣ ከዚህ ቀደም ለወላይታ ድቻ (ብሔራዊ ሊግ) , አየር ሀይል ,ሀዋሳ ከነማ , ደደቢት,ፋሲል ከነማ መጫወቱ እሚታወስ ነው

Managing Editor at Hatricksport Website

FacebookTwitterGoogle+YouTube

ሙሴ ግርማይ

Managing Editor at Hatricksport Website