ፋሲል ከተማ በመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬ ላይ ከድሬደዋ ከተማ ጋር 1አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ባጋጠመው ከፍተኛ ጉዳት ከሦስት ወራት በላይ ከሜዳ መራቁ የሚታወስ ነው።
ተጫዋቹ ከጉዳቱ ለማገገም ከፍተኛ የሆነ የህክምና ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ባሁን ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ በመገኘቱ በነገው እለት ልምምድ እንደሚጀምር ታውቋል።

አይናለም ሀይለ ፋሲል ከተማ በሁለተኛው ዙር 16ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራትን በአዲስአበባ ስታዲየም እሚያስተናግድ ሲሆን በጨዋታ ላይ ከስብስቡ ውጪ መሆኑ ክለቡ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።
አስተያየት ይስጡ