መነሻ ገጽ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርተዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባጅማ አባጅፋርፋሲል ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

 

በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከተማ ጨዋታ 0-0 በሆነ ውጤት ፍፃሜውን አግንቷል።

በጅማ አባጅፋር በኩል ሰሑል ሽረን አቻ ያወጣውን ስብስብ ይዘው ሲገቡ ፋሲል ከነማዎች በሜዳቸው ሲዳማ ቡናን ካሽነፈው ስብስብ ኦሲ ማውሊን በማሳረፍ ኪሩቤል ኅይሉን ተክተው ገብተዋል።

 

ሳቢ በነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ እንቅስቃሴ ተመጣጣኝ ጨዋታ እና ብዙ የግብ መከራዎች የታዩበት ነበር። በመጂብ ቃሲም እና ኢዚ አዙካ ጫና በፈጠሩባችው የመጀመሪያዎቹ ሀያ አምስት ደቂቃዎች ለግብ የቀረቡ መካሪዎች አድርገዋል። ከነዚህም በመጀመሪያው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ሱሪፌል ዳኛችው ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ለግብ የቀረበ ሙከራ እና በተደጋጋሚ ሱራፌል ዳኛችው ከሳጥን ዉጪ አክርሮ የመታቸው ኳሶች ይጠቀሳሉ። ሙጂብ ቃሲም ሽመክት ጉግሳ ያሻገረለትን ኳስ መቶ የግቡን ቋሚ ታካ የወጣችው ኳስ ፋሲል ከነማን መሪ ለማድረግ የተቃረበች የግብ አጋጣሚ ነበረች። ጨዋታው እንደ ተጀመረ ወደ ማጥቃት እቅስቃሴ የገቡት ጅማ አባጅፋሮች በተለይም በሰምንትኛው ደቂቃ ላይ መላኩ ወልዴ የመታት ቅጣት ምት ኤፍሬም ጌታችው ከግብ ጠባቂው ሚኬል ሳማኪ ጋር አንድ ለአንድ ተግናኝቶ አገባው ተበሎ ሲጠበቅ ሳይጠቀምበት የቀረው ኳስ እና በመጨረሻዎቹ አስር ደቂቃዎች ጫና በመፍጠር ያለቀላቸው የግብ ዕድሎች መፍጠር ችለዋል። በሁለቱም ቡድኖች በኩል ምንም ግብ ሳይስተናገድ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።


ከመጀመሪያው አጋማሽ በቁጥር የነሱ ሙከራዎችን የታየበት ሁለቱም ቡድኖች በብዙ ረገድ የወረደ እንቅስቃሴ ያደረጉበት ነበር። ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ንፁህ የግብ ዕድል የፈጠሩበት አጋጣሚዎች ነበሩ። በሁለትኛው አጋማሽ የመጀመሪያዎቹን አስራ አምስት ደቂቃዎች የተሻለ የኳስ ቅብብል በማድረግ እና ወደ ጎል በመቅረብ በኩል ጅማ አባጅፋሮች የተሻሉ ነበሩ። 61ኛው ደቂቃ ላይ ኤሊያስ አህመድ ለጀሚል ያቁብ አቀብሎት ጀሚል የሞከራትን እና የፋሲል ከነማው ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኪ ያዳነበት አጋጣሚ በጅማ አባጅፋር በኩል የምታስቆጭ ዕድል ነበረች።

ፋሲል ከነማዎችም ጨዋታውን አሸንፎ ለመወጣት ያለሙ መካሪዎች አድርገዋል በተለይም ኢዙ አዙካ የግብ ጠባቂው ሰኢድን መወጣት ተመልክቶ ወደ ግብ ቢመታትም ብረቱን ለትማ የመለሰችው ኳስ አስቆጪ መከራ ነበር። ውጤቱ 0-0 በመጠናቀቁን ተከትሎ ጅማ አባጅፋሮች ነጥባቸውን ወደ 12 ከፍ ቢያደርጉም ወድ 15ኛ ደረጃ ዝቅ ሊሉ ችለዋል። ፋሲል ከነማ ከመሪው ጋር የነበራቸው የነጥብ ልዩነት ይበልጥ የመጥበብ ዕድላቸውን አምክኗል በእንድ ደረጃ ዝቅ ብለዋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...