የጨዋታ ዘገባ | የጅማ አባጅፋር እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ መጨረሻ ላይ በተቆጠሩ ግቦች በአቻ ውጤት ተጠናቋል

 

በአስራ ሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል፡፡

ጅማ አባ ጅፋር ሳምንት ከበባህር ዳር ሽንፈት ከተመለሰበት የመጀመሪያ ተሰላፊዎች ውስጥ ኤልያስ አታሮ ፣ ተመስገን ደረሰ እና ኤርሚያስ ኃይሉን በማሳረፍ ለመላኩ ወልዴ፣ አመረላ ደልታታ እና ሱራፌል ዐወል የመሰለፍ ዕድል ሰጥቷል። ኢትዮጵያ ቡናዎች ደግሞ በ16ኛው ሳምንት ስሑል ሽረን ከረታው ቡድናቸው ውስጥ ኃይሌ ገብረተንሳይ እና ዓለምአንተ ካሳን በአህመድ ረሻድ እና ሬድዋን ናስር ተክተው ጨዋታውን ጀምረዋል።

የመጀመሪያው አጋማሽ በኢትዮጵያ ቡና ግልፅ የሆነ የማጥቃት ፍላጎት ይዘው ነበር የገቡትእንዲሁም በጅማዎች የመልሶ ማጥቃት አቀራረብ ነበር ጨዋታውን ለመሸነፍ የገቡት። ኢትዮጵያ ቡናዎች የተሻለ የማጥቃት ኃይላቸውን ይዘው የገቡበት በተቃራኒው ጅማ አባጅፋሮች በ35ኛው ደቂቃ ላይ አምረላ ደልታታን በጉዳት ካጡ በኃላ ለማጥቃት የነበራቸው ፍላጎት ቀዝቀዝ ብሎ የታየበት ነበረ፡፡ ቡናማዎቹ በርካታ አጋጣሚዎች ቢያገኙም ግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ ግብ ከመሆን ታድጓቸዋል፡፡

የሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከመጀመሪያው አንፃር በግብ ሙከራዎች እንዲሁም በእንቅስቃሴ ለውጥ ያላሳየ ነበር።
ቡናማዎቹ በአቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንን ያለቀላቸውን አጋጣሚዎች ቢያገኙም የጅማው ግብ ጠባቂ ሰይድ ሀብታሙ አድኖባቸዋል፡፡


ጨዋታው ወደ ማገባደጃው ላይ 89ኛ ደቂቃ ላይ የጨዋታው የመጀመሪያ ጎል መቆጠር ችለዋል። በቀኝ መስመር ኳስ እየገፋ የገባው ሚኪያስ መኮንን ወደ ጅማ የግብ ክልል ያሻማውን ኳስ በግሩም የግንባር ጎል ኢትዮጽያ ቡናዎች በአቡበከር ናስር አማካይነት ማስቆጠር ችለዋል።

ከግቡ መቆጠር በኃላ ጨዋታውን በፍጥነት የጀመሩት ጅፋሮቹተመስገን ደረስ የመታውን ከስ
የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ ስህተት ታክሎበት ኤርምያስ ኃይሉ ያገኘውን ዕድል ወደ ግብ ቀይሮ ጅማ አባ ጅፋር ነጥብ መጋራት ችለዋል።

ጨዋታው 1-1 መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና 21 ነጥብ በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ ጅማ አባ ጅፋር በ19 ነጥብ በወራጅ ቀጠናው ለመቆየት ተገዷል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer