በአስራ ሁለተኛው ሳምንት የሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም በአዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል የሚደረገው ጨዋታ ዋነኛው ነበር ::
ከጨዋታው ጅማሮ አስቀድሞ በጉዳት ላይ ለምተግኘው የቀድሞው የደደቢት ሴት እግር ኳስ ተጫዋች ቤዛዊት ታደሰ የህክምና ወጪን አስመልክቶ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በሉሲዎች ተጫዋቾች ሴናፍ ዋቁማ ሰናይት ቦጋለ እና ሌሎችም ተደርጓል ::
በደጋፊዎች ደማቅ ህብረ ዝማሬ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እንደ ሁሌውም ኳስን መሰረት አድርገው መጫወትን ምርጫቸው ሲያደርጉ ኳስን መስርተው ከኋላ ለመውጣት ባሰቡበት ሰአት የሰሩትን ስህተት ተከትሎ ከነአን ማርክነህ አስደንጋጭ ሙኩራ ቢያደርግም ግብ ጠባቂው በረከት አማረ ሊያድንበት ችሏል ::

ከደቂቃዎች በኋላ የተከላካዮችን ስህተት የተጠቀሙት አዳማዎች ከግራ መስመር የተሻማውን ኳስ ዳዋ ሆቴሳ ከመረብ ላይ በማዋሀድ አዳማዎችን መሪ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል ::
ከመስመር በሚነሱ ኳሶች የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ያደረጉት አዳማዎች ከጎሉም መቆጠር በሃላ ከመስመር በተሻገረ ካስ ከነአን ማርክነህ አስደንጋች ሙከራ ቢሞክርም በግቡ አግዳሚ ታካ ወጥታለች ::

ከጎሉ መቆጠር በኋላ አሰደንጋጭ መኩራ ማደረግ የተሳናቸው ቡናዎች የኳስ እንቅስቃሴው በሁለቱም ቡድኖች መካከል በመሀል ሜዳው ላይ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተገድቦ ታይቷል ::
በመስመር በኩል የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ያደረጉት አዳማዎች በእለቱ ሙከራዎችን ሲያደርግ በነበረው ከነአን ማርክነህ ከሳጥን ውጪ አክርሮ በመታት ኳስ መሪነታቸውን ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችለዋል ::
ከሁለቱ ጎል መቆጠር በኋላ አፈግፍገው መጫወት የፈለጉት አዳማዎች ኢትዮጵያ ቡናዎች በበኩላቸው ከመጀመሪያዎች አስራ አምስት ደቂቃዎች በተሻለ መልኩ ሲያጠቁ ተስተውለዋል ::

የኢትዮጵያ ቡና የማጥቃት እንቅስቃሴ በይበልጣ በግራ መስመር በአስራት ቱንጆ በኩል አመዝኖ ታይቷል ::
ቡናዎች ከማእዘን ምት በተነሳ ሙከራ ሳጥን ውስጥ ፈቱዲን ጀማል አክርሮ መቶት የግቡ አግዳሚ የመለሰበት አጋጣሚ በቡናዎች በኩል በመጀመሪያው አጋማሽ ከሚያስቆጩ አጋጣሚዎች መካከል ዋነኛው ነበር ::
የመጀመሪያው አጋማሽም ብዙም ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ሳይታዩበት ሊጠናቀቅ ችሏል ::
በሁለተኛው አጋማሽ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ሲታይ ሙከራዎችን ለማድረግ በሁለቱም ቡድኖች በኩል በርካታ ደቂቃዎች ወስዶባቸዋል :: የመጀመሪያውን አስደንጋጭ ሙከራም ማድረግ የቻሉት ቡናዎች ሲሆኑ ከሳጥን ውጪ እንዳለ ደባልቄ አቀብሎት ታፈሰ ሰሎሞን ሳይጠቀምበት የቀረው በኢትዮጵያ ቡና በኩል ከሚጠቀሱ ሙከራዎች አንዱ ነው ::

በአዳማ ከተማ በኩል በመልሶ ማጥቃት ሄደው ከመስመር ለዳዋ ሆቴሳ ተሻግሮለት አማኑኤል ዮሐንስ ደርሶ ያዳናው ተጠቃሹ ነው ::
በመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ በተገደበው ጨዋታ የመልሶ ማጥቃት አጫዋወትን የመረጡት አዳማ ከተማዎች መሪነታቸውን ያሰፉበትን ጎል በቡልቻ ሹራ አማካኝነት አስቆጥረዋል ::
በመልሶ ማጥቃት ከመስመር ይዘውት የገቡትን ኳስ ቡልቻ ሹራ ሱሌማን ሰሚድን አቀብሎት መሪነታቸውን ያጠናከሩበትን ጎል ማስቆጠር ችለዋል ::

አዳማዎች ከጎሉ መቆጠር በኋላ አጥቅተው መጫወታቸውን ሲቀጥሉ ዳዋ ሆቴሳ ከሳጥን ውጪ ሞክሮ በግቡ አግዳሚ ታካ የወጣችው ኳስ የምትጠቀስ ነበር ::
ጨዋታው በአዳማ ከተማ የበላይነት ሲጠናቀቅ በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ ሲቀመጡ ኢትዮጵያ ቡናዎች በወራጅ ቀጠናው አስራ አራተኛ ላይ ተቀምጠዋል ::

አስተያየት ይስጡ