የጨዋታ ዘገባ| ሲዳማ ቡና በይገዙ ቦጋለ ግብ ከሜዳ ውጭ ድል አድርጓል

 

የ14ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ሲዳማ ቡና ወደ ወልቂጤ አምርቶ በይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ግብ ወልቂጤ ከተማን 1-0 በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

ክትፎዎቹ ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ አቅንተው ከኢትዮጵያ ቡና ነጥብ የተጋሩበትን አሰላለፋቸው የአንድ ተጫዋች ላይ ለውጥ በማድረግ በረከት ጥጋቡን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመልሱ። ሲዳማ ቡናዎች ደግሞ አዳማን ካሸነፈው ስብስባቸው የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገው አዲስ ግደይ እና ግሩም አሰፋ ይዘው ገብተዋል።

በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ በሁለቱም በኩል ረጃጅም ኳሶች ሲጠቀሙ የተስተዋለ ሲሆን። በተለይ ሲዳማ ቡናዎች ኳስ ይዘው ለመጫወት ፍላጎት ቢናኖራቸውም ሜዳው ኳስ ለማንሸራሸር አመቺ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ረጃጅም ኳሶች እንዲጫወቱ አስገድዷቸዋል። ክትፎዎ በበኩላቸው ኳሶችን በሚያገኙበት ስአት በቀጥታ ወደ ፊት በማሻገር ለአህመድ ሁሴን እና ሳዲቅ ሴቾ በማድረስ የግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል። በሙከራ ደረጃ ቀዳሚ የነበሩት ባለሜዳዎቹ ሳዲቅ ሴቾ በቅጣት ምት የተገኘችውን ኳስ ተጠቅሞ ለኤፍሬም ዘካርያስ አቀብሎት ኳሷን ሙሉ በሙሉ ሳያገኛት ቀርቶ ወደ ውጭ የወጣችበት ነበረች። ከመሀል ሜዳ የተሻገረችለትን ረጅም ኳስ አዲስ ግደይ ኳሷ ላይ ከመድረሱ በፊት ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔ ከግቡ ወጥቶ ባከሸፈበት አጋጣሚ ወደ ግብ መድረስ የጀመሩት እንግዳዎቹ። 8ኛው ደቂቃ ላይ ይገዙ ቦጋለ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ችለዋል።

ደቂቃዎች እየገፉ በሄዱ ቁጥር በሁለቱም ቡድኖች በኩል ሀይል የተቀላቀለበት ረጃጅም ኳሶች ሲጫወቱ። የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ተጎድተናል በማለት ሜዳ ላይ እየተኙ ደቂቃዎች ሲገድሉ ተስተውሏል። በዚህ አጋማሽ ፍፁም ተረጋግተው ጨዋታቸውን ለማድረግ የተቸገሩት ባለሜዳዎች በርካታ አጋጣሚዎችን ቢፈጥሩም ኳስ እና መረብን ለማገናኘት ተቸግረዋል። አህመድ ሁሴን በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ ፍቅሩ ወዴሳ የተቆጣጠበት። ኤፍሬም ዘካርያስ የመታውን ኳስ ፍቅሩ ወዴሳ እንደምንም ያወጣበት እና ጫላ ተሺታ ተቀልብሶ መቶት ወደውጭ ወጣ የወጣችበት ማሳያ ነበሩ። ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳይታከልበት በሲዳማ ቡናዎች 1-0 መሪነት ለእረፍት አምርተዋል።

በሁለኛው አጋማሽ ወልቂጤ ከተማዎች ኳስን ተቆጣጥረው ሲጫወቱ ሲዳማ ቡናዎች በአንፃሩ እንደ መጀመሪያው ግማሽ የረጃጅም ኳሶችን አጨዋወት ተግባራዊ አድርገዋ። ቶማስ በረጅሙ የመታው ኳስ አህመድ ሁሴን በግንባሩ ገጭቶት ለጥቂት ወደ ውጭ ስትወጣበት። አዳነ በላይነህ ያደረጋትን ሙከራ ግብ ጠባቂው ፍቅሩ ወዴሳ ከግቡ ወጥቶ የወጣበት ኳስ ተጠቃሽ ጥሩ ሙከራዎች ናቸው።

ወልቄጤ ከተማዎች አጥቅተው ለመጫወት በማሰብ የተከላካይ መስመራቸውን በመቀነስ በሶስት ተካላካዮች ሲጫወቱ። ሲዳማ ቡናዎች ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከተጋጣሚያቸው የሚሰነዘሩባቸውን ጥቃቶች በመመከት ላይ ተጠምደው ሲስተዋሉ ነበር። አሳሪ አልማህዲ በቅጣት ምት የተገኘችውን ኳስ በቀጥታ ወደግብ መትቶ ለጥቂት በአግዳሚ የወጣችበት በክትፎዎቹ በኩል አስደንጋጭ ሙከራ ነበረች። እንግዳዎቹ ይህ ነው የሚባል አጋጣሚ ያልፈጠሩ ሲሆን። ክትፎዎቹ በበኩላቸው ሳዲቅ ሴች ሳይጠቀምባት የቀረችው የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር። ጨዋታው በሲዳማ ቡና 1-0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ። ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ወልቂጤዎች በዚህ አመት በሜዳቸው ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግደዋል።