መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ቅ/ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ዳሰሳኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ቅ/ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የዕለተ ቅዳሜ ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ (ቅዳሜ) አንስቶ እስከመጪው ረቡዕ ድረስ በአ/አ እና በክልል ስታዲየሞች የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

ወላይታ ሶዶ ላይ በሊጉ ደካማ አቋም ያሳየው እና ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስንብት በኋላ መነቃቃት ያሳየው ወላይታ ድቻ እስካሁን በሊጉ ሽንፈት ያላስተናገደውን የአምናውን ሻምፒዮን ቅ/ጊዮርጊስን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

በ12ኛው ሳምንት የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አ.ዩ. ጋር ተጫውተው 1-1 አቻ የተለያዩ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ ከደደቢት ጋር አ/አ ስታዲየም ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት በቂ የፀጥታ ሀይል የለም በመባሉ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታውን ሳያከናውን ለዚህኛው ጨዋታ ወደ ሶዶ አቅንቷል።

ወላይታ ድቻ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ካደረጋቸው 5ጨዋታዎች መካከል ሁለቱን ማለትም ኢትዮ-ኤሌክትሪክን 2-0 እንዲሁም አርባምንጭ ከተማን 1-0 በማሸነፍ በአንዱ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር 1-1 አቻ ወጥቶ በሁለቱ ማለትም በአዳማ ከተማ 2-1 እንዲሁም በመቐለ ከተማ 1-0 ተሸንፏል።

ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ ማድረግ ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 5ቱን ከሜዳው ውጪ ያከናወነ ሲሆን ዛሬ ወደ ሶዶ ተጉዞ ከወላይታ ድቻ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ 6ኛው ይሆናል። ቅ/ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡናን 1-0 እንዲሁም ጎንደር ላይ ፋሲል ከተማን 2-0 በማሸነፍ አ/አ ላይ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር(ባለሜዳው ኢትዮጵያ ቡና ነበር።)፣ አዲግራት ላይ ከወልዋሎ አ.ዩ. ጋር እንዲሁም ወልድያ ላይ ከወልዲያ ከተማ ጋር ያለግብ 0-0 መለያየት ችሏል። ይህንን ተከትሎ ቅ/ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ግብ ያላስተናገደ ክለብ ያደርገዋል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን አሰናብቶ ዘነበ ፍሰሀን እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ቋሚ አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ወላይታ ድቻ በአጠቃላይ ማድረግ ከነበረበት 12 ጨዋታዎች አድርጎ ሶስቱን አሸንፎ በአምስቱ አቻ ተለያይቶ በአራቱ ተሸንፎ ማግኘት ከነበረበት 36 ነጥቦች 13ቱን ብቻ አሳክቶ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ቅ/ጊዮርጊስም ከ12 ጨዋታዎች 10 ጨዋታዎችን አድርጎ አምስቱን በማሸነፍ አምስቱን አቻ ወጥቶ ያለምንም ሽንፈት ከመሪው ደደቢት በ5 ነጥቦች ርቆ በ20 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

የሁለቱን ቡድኖች የ2009ዓ.ም ግንኙነት ካየን በ7ኛው ሳምንት ታህሳስ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን በጨዋታውም ቅ/ጊዮርጊስ በአቡበከር ሳኒ እና አዳነ ግርማ ግቦች ታግዞ 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ከቅ/ጊዮርጊስ በኩል ረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የሚገኙት ሰልሀዲን ሰዒድ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ አሜ መሀመድ፣ አዳነ ግርማ፣ አሉላ ግርማ እና ታደለ መንገሻ አሁንም ለቡድኑ ግልጋሎት አይሰጡም። አዲሱ ፈራሚ ጋዲሳ መብራቴ ከጉዳቱ ቢያገግምም የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። በወላይታ ድቻ በኩል ፀጋዬ ብርሀኑ በጉዳት እንዲሁም ተስፉ ኤልያስ በቅጣት እዚህ ጨዋታ ላይ አይገኙም።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወላይታ ሶዶ ላይ በወላይታ ሶዶ ስታዲየም ዛሬ (ቅዳሜ) 9፡00 ሲል የሚጀምር ይሆናል።

ጨዋታውን የሚመሩት ዳኛ፡- ለሚ ንጉሴ

በሌላ የዕለተ ቅዳሜ የክልል ጨዋታ 10:00 ሲል ድሬ ላይ በውጤት ቀውስ ውስጥ ያሉት ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ቡና ካለፉት 5ጨዋታዎች አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፈ ሲሆን በ3ቱ ተሸንፎ በአንዱ ደግሞ አቻ ወጥቶ በሊጉ ቁልቁል መውረዱን ተያይዞታል። ድሬዳዋ ከተማ በአንፃሩ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ካሰናበተ በኋላ በምክትል አሰልጣኙ ስምኦን አባይ እየተመራ የውጤት መሻሻሎችን እያስመዘገበ ይገኛል።

በ12ኛው ሳምንት የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማም ሆነ ኢትዮጵያ ቡና አ/አ ስታዲየም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት በቂ የፀጥታ ሀይል የለም በመባሉ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ሳያከናውኑ ነው ለዚህኛው ጨዋታ ወደ የቀረቡት።

ድሬዳዋ ከተማ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ካደረጋቸው 5ጨዋታዎች መካከል በኩዋሜ አትራም ብቸኛ ግብ ጅማ አባጅፋርን 1-0 ያሸነፈበት ጨዋታ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያስመዘገበው ብቸኛው ድሉ ሲሆን በቀሪዎቹ በ4ቱ ጨዋታዎች ማለትም ከደደቢት እና ከአዳማ ከተማ ጋር በተመሳሳይ 0-0 እንዲሁም ከፋሲል ከተማ እና ከሲዳማ ቡና ጋር በተመሳሳይ 1-1 አቻ የወጣ ሲሆን በሜዳው እስካሁን ሽንፈት አላስተናገደም።

ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች 5ቱን ከሜዳው ውጪ ያከናወነ ሲሆን ዛሬ ወደ ድሬ ተጉዞ የሚያደርገው ጨዋታ 6ኛው ይሆናል። ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አ/አ ስታዲየም ላይ በኢትዮ-ኤሌክትሪክ 2-1(ባለሜዳው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ነበር።)፣ አዲግራት ላይ በወልዋሎ አ.ዩ. እንዲሁም በደደቢት በተመሳሳይ(ባለሜዳው ደደቢት ነበር።) 1-0፣ አዳማ ላይ በአዳማ ከተማ 2-1 ጅማ ላይ በጅማ አባጅፋር 2-0 ተሸንፏል። ይህም ማለት ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮው የውድድር አመት ከሜዳው ውጪ አንድም ነጥብ ማስመዝገብ አልቻለም።

በአጠቃላይ ድሬደዋ ከተማ ማድረግ ከነበረበት 12 ጨዋታዎች 10 አድርጎ አንዱን ብቻ አሸንፎ በስድስቱ አቻ ተለያይቶ በሶስቱ ተሸንፎ ማግኘት ከነበረበት 30 ነጥቦች 9ኙን ብቻ አሳክቶ 14ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ቡና ከ12 ጨዋታዎች 11 ጨዋታዎችን አድርጎ ሶስቱን በማሸነፍ ሶስቱን አቻ ወጥቶ በአምስቱ ተሸንፎ በ12 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

የሁለቱን ቡድኖች የ2009ዓ.ም ግንኙነት ካየን እንደ ቅ/ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ ሁሉ በ7ኛው ሳምንት ታህሳስ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን ጨዋታቸውንም ያለግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

ከኢትዮጵያ ቡና በኩል አክሊሉ አየነው እና፡ቶማስ ስምረቱ በጉዳት ለቡድኑ ግልጋሎት አይሰጡም። በወልዲያ ከተማ በኩል ይህ ቅድመ ዳሰሳ እስከተሰራበት ሰዓት ድረስ የተሰማ የጉዳትም ሆነ የቅጣት ዜና የለም።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ድሬ ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ዛሬ (ቅዳሜ) 10፡00 ሲል የሚጀምር ይሆናል።

ጨዋታውን የሚመሩት ዳኛ፡- ማኔ ወ/ፃዲቅ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...