የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ድሬዳዋ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ

 

የ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት (አርብ) መከናወን የጀመሩ ሲሆን ነገ (እሁድ) ደግሞ 5ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ 5ጨዋታዎች መካከል ድሬ ስታዲየም ላይ ድሬዳዋ ከተማ መቐለ 70 እንደርታን የሚያስተናግድበት ጨዋታ የሚጠበቅ ነው።

ጨዋታ: ድሬዳዋ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ
የጨዋታ ቀን: እሁድ የካቲት 15/2012
የጨዋታ ቦታ: ድሬ ስታድየም
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ሄኖክ አክሊሉ

ድሬዳዋ ከተማ በዘንድሮው ውድድር ወጣ ገባ የሚል አቋም እያሳየ የሚገኝ ሲሆን በውጤት መዋዠቅ ምክንያት አሰልጣኞችን ካሰናበቱ ክለቦች አንደኛው ነው። እጅግ ደካማ ብቃት እያሳየ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ካለፉት 5ጨዋታዎች ድል ማድረግ የቻሉት በአንዱ ብቻ መሆኑ ሁኔታዎችን ከባድ ያደርግባቸዋል።

በድሬዳዋ በኩል በዘንድሮው የውድድር አመት የፍሬድ ሙሸንዲ፣ ኤልያስ ማሞ እና የሪችሞንድ ኦዶንግ ብቃት ጥሩ ሁኔታ ላይ ቢገኝም እጅግ ደካማ የሆነው የተከላካይ ክፍሉ ግን ድሬዳዋን አሁን ለሚገኝበት ደረጃ ዳርጎታል።

ተጋጣሚው የአምናው ሻምፒዮን መቐለ 70 እ. በአንፃሩ እንደ አምናው ወጥ ብቃት ማሳየት ቢሳነውም በተሐይ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በጥሩ ብቃት በማሸነፍ ከመሪዎቹ ላለመራቅ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በመቐለ በኩል ባለፈው ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ላይ ሀትሪክ መስራት የቻለው ኦኪኪ አፎላቢ ለደካማው የድሬዳዋ ከተማ ከባድ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል። ከሱ በተጨማሪም የአማኑኤል ገ/ሚካኤል አስፈሪነት ሌላው ፈተና ይሆናል።

ድሬዳዋ ከተማ በዘንድሮው ውድድር ካደረጋቸው 14ጨዋታዎች መካከል 6ጨዋታዎችን ሲያደርግ 3ጨዋታዎችን ድል ሲያደርግ በ2ጨዋታዎች አቻ ወጥቶ በ1 ጨዋታ ብቻ ሽንፈት አስተናግዷል።

እንግዳው መቐለ 70 እ. 6ጨዋታዎችን ከሜዳው ውጪ ያደረገ ሲሆን በ4ጨዋታዎች ተሸንፎ በቀሪዎቹ 2ጨዋታዎች ድል ማድረግ ችሏል። ይህም የአምናው ሻምፒዮን ከሜዳው ውጪ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ምን ያህል እንደሚከብደው ያሳያል።

ፌደራል አርቢትር ሄኖክ አክሊሉ በሚመሩት ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ያሬድ ታደሰ፣ በረከት ሳሙኤል እና ረመዳን ናስር በጉዳት የማይገቡ ሲሆን ያሬድ ከበደ እና ሚካኤል ደስታ ደግሞ መቐለ 70እንደርታን በነገው ጨዋታ ማገልገል አይችሉም።

Muluken Tesfaye

Editor at Hatricksport website

Facebook

Muluken Tesfaye

Editor at Hatricksport website