የጨዋታ ቅድመ – ዕይታ | ባህርዳር ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ቅድመ ዕይታ | ባህርዳር ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሁለት ሳምንት አረፍት በኋላ ዛሬ ጅማሮውን ሲያደርግ ነገም ቀጥሎ 6 ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። በባህርዳር አለማቀፍ ስታድየም ሚካሄደው የባህርዳር ከተማና የጅማ አባጅፋር ጨዋታ እንደሚከተለው ዳስሰነዋል።

ጨዋታ: ባህርዳር ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር
የጨዋታ ቀን: እሁድ የካቲት 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ማኑሄ ወልደፃዲቅ
የጨዋታ ቦታ: ባህርዳር አለማቀፍ ስታድየም

በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት ያላስተናገዱት የጣናው ሞገዶች በቅርብ ጨዋታዎች ከሜዳው ለተጋጣሚው በቀላሉ እጁን የማይሰጠው ጅማ አባጅፋርን የሚያስተናግድበት ይህ ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል። በዝውውር መስኮቱ እስካሁን ምንም ተሳትፎ ያላደረጉት ሁለቱም ቡድኖች። በነገው ጨዋታ ባህርዳሮች በሜዳው እንደሚጫወት ቡድን መጠን ኳስን መሰረት አድርጎ ሁሌም በሜዳው ተግባራዊ የሚያደርገው ከመሀል ሜዳ በሚነሱ ኳሶች የግራ እና ቀኝ መስመር ተጠቅመው ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ አጋጣሚዎችን ይፈጥራሉ ተብሎ ሲጠበቅ ተጋባዦቹ ከሜዳቸው ውጭ በብዛት የሚተገብሩት የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ይከተላሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ወደ ሊጉ ያራደጉት ባርዳር ከተማ በተቃራኒ የሚገጥሙ ጨዋታ ነው። የጣናው ሞገዶች በሜዳቸው ምንም ሽንፈት ያላስተናገደ ቡድን መሆኑን ተያይዞ የማሸነፍ ግምቱ ወደነሱ ቢያዘነብልም የተጋጣሚው ወቅታዊ አቋም ግን በቀላሉ ነጥብ ይዞ ለመውጣት እንደሚቸገሩ ምንም አያጠራጥርም። የነበረባቸውን የተከላካይ ችግር በዚህኛው ዙር ባህርዳሮች ቀርፈው የማይመለሱ ከሆነ ወጋ መክፈላቸው የማይቀር ጉዳይ ሲሆን ጠንካራው የተጋጣሚ ተከላካይ ስፍራ መስበር ይጠበቅባቸዋል።

ጉዳት እና ቅጣት

ባህርዳር ጉዳት – ፍቅረሚካኤል አለሙ ፤ ወሰኑ አሊ እና ማማዱ ሲዲቤን   በጉዳት ምክነያት ሲሆን በጅማ በኩል አሌክስ አሙዙ እና አብርሀም ታምራት በቀይ ካርድ እና መላኩ ወልዴ በአምስት ቢጫ ወደ ስፍራው ያልተጓዙ ሲሆን በተጨማሪም የያኩቡ መሀመድ እና መሀመድ ሙንታሪ ክለቡን ባለ መቀላቀላቸው ወደ ስፍራው አልተጓዙም። በሰርግ ምክኒያት ያለፉትን ሁለት ጫወታዎች ያልነበረው ሰዒድ እና ጉዳት ላይ የነበረው አምረላ ደልታታ የመሰለፍ እድል ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

የእርስ በእርስ ግኑኝነት

በ2011 የጀመረው የሁለቱም ቡድኖች ግንኝነት በሊጉ ሶስት ግዜ ተገናኝተው ጅማ አባጅፋር አንዱን አሸንፏል። በቀሪው ሁለት ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ባህርዳር ከተማ አንድ ጅማ አባጅፋር ሁለት ጎሎችኝ አስቆጥረዋል።ይህ ጨዋታ ባህርዳር ላይ በፌደራል አርቢትር ማኑሄ ወልደፃዲቅ እየተመራ 9:00 ይጀመራል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer