የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል

 

በደሞዝ አለመከፈል ምክንያት ዛሬ ጠዋት ልምምድ አቁመው የነበሩት የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ዛሬ ከሰዓት ወደ መደበኛ ልምምዳቸው መመለሳቸው ታውቋል። በተደጋጋሚ ሲጠይቁት የነበረው የደሞዝ የይከፈለን ጥያቄ ባለመመለሱ ልምምድ ሊያቆሙ መገደዳቸውን እና እንዳቆሙም ጭምር በድረገፃችን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ጠዋት ላይ የክለቡ የበላይ አካላት በወሰዱት አፋጣኝ ምላሽ እና በቅርብ ቀናት ውስጥ ተፈፃሚ እናደርጋለን በማለታቸው ተጫዋቾቹ ወደ መደበኛ ልምምዳቸው የተመለሱ ሲሆን በቀጣዩ እሁድ ጅማ አባጅፋር በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን በ14ኛ ሳምንት ለመግጠም ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ጀምረዋል፡፡

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer