የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች መደበኛ ልምምዳቸውን አቋርጠዋል።

 

የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች በደሞዝ ምክንያት ልምምዳቸውን አቁመዋል።

 

ጅማዎች ባለፈው ሳምንት ድሬደዋ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ቢችሉም አሁንም የቡድኑ ውስጣዊ ችግር አለመፈታት በቀጣይ ጉዟው ላይ ዳግም እንቅፋት እንዲፈጥርባቸው አድርጓል። የደሞዝ ጥያቄው አለመፈታቱን ተከትሎም የቡድኑ አባላት ልምምዳቸውን ካቋሙ ሁለት ቀን የሆናቸው ሲሆን ሲሆን በቀጣይ አርብ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ሀዋሳ የመጓዛቸው ጉዳይ በውል አለየለትም። ችግሩ በቶሎ የማይቀረፍ ከሆነ በርካታ
ተጫዋቾች ከቡድኑ ሊለቁ እንደሚችሉ ሰምተናል። ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ይመለሱ ይሆን?

ሰለቡድኑ እና በክለቡ ያሉ አዳዲስ ነገሮችን
እየተከታተልን እናቀርባለን።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer