የድሬዳዋ ከተማ 6 የሚደርሱ ተጨዋቾች በወባ በሽታ
ተጠቅተዋል ጠንከር ያለ ህመም ያጋጠመው ወሰኑ ወደ አዲስ አበባ መጥቷል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ድሬዳዋ ከተማ ለመጫወት የተዘጋጁ 6 የሚደርሱ ተጨዋቾች ከቀናቶች በፊት ባጋጠማቸው የወባ በሽታ ጥቃት ጉዳት ላይ የደረሱ ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓትም ተጨዋቾቹ ድሬዳዋ ላይ ህክምና እያደረጉ
መሆኑ ታውቋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ክለብ ተጨዋቾችን ያጋጠማቸው የወባ በሽታ ደንጌ በሚል ስም እንደሚጠራ የተገለፀ ሲሆን ይህ ህመም ካጋጠማቸው ውስጥ ወሰኑ ማዜ ቀስቴ አህመድ ረሺድ ሺሪላ ዬሴፍ ዳሙዬ በረከትና የመሳሰሉት ተጨዋቾች ሲሆኑ እነዚህ ህክምና እየወሰዱ ካሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ወሰኑ ላይ የደረሰው ህመም ጠንከር በማለቱ በጉሉኮስ ሆኖ ሁሉ ሲታከም የነበረ ሲሆን ተጨዋቹ የአሁን ሰዓት ላይም ወደ
አዲስ አበባ መጥቶ ህክምናውን እያደረገ መሆኑና አሁን
በጤናው ላይ ለውጥ እያመጣ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ድህረገፅ ለእነዚህ ተጨዋቾች ፈጣሪ ምህረቱን ሰጥቷቸው ወደ ጤንነታቸው እንዲመለሱ ይመኛል፡፡
አስተያየት ይስጡ