የክለብ ፕሬዝዳንቱ ለኮረና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ዝግጅት የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ

 

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አለምን እያመሰ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት የተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በሽታውን ለመዋጋት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህ መካከልም ስፖርቱ ላይ የሚገኙ የተለያዩ አካላት ድጋፋቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይጠቀሳሉ። ከነዚህ በተጨማሪም የወልቂጤ ከነማ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አበባዉ ሰለሞን ለኮረና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ዝግጅት የ100 ሺህ ብር ድጋፍ ለከተማዉ ጤና ጽህፈት ቤት በማበርከት ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። ወጣት ሰለሞን የ100 ሺህ ብር ድጋፉን ለወልቂጤ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት በዛሬው እለት ማስረከብ ችለዋል።

የዚህን ወጣት አርአያነት በመከተል ሌሎች በስፖርቱ አካባቢ የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ይህንን በሽታ ለመከላከል ርብርብ ማድሰግ እንደሚገባቸው ሀትሪክ ስፖርት ታምናለች።